ዓለም ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ በትራንስፖርት እና በመንገድ ደህንነት ማሻሻያ ትግበራ የ200 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነድፎ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
Hidaya Shemsu2021-04-09T07:37:03+00:00የፕሮጀክቱ አካል የሆነ እና ለትራፊክ ፍሰት እንዲሁም ለሰላም እና ጸጥታ ስራ የሚያግዙ 17 ፓትሮል ተሸከርካሪዎችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል፡፡በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ ተሸከርካሪዎቹን አስረክበዋል፡፡በመርሃ ግብሩ በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ እንደገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል አለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነድፎ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ዛሬ ርክክብ የተደረገባቸው 17 ፓትሮል ተሸከርካሪዎችን የፕሮጀክቱ አንዱ አካል መሆናቸውን ሚስስ ዳይና ገልጸዋል፡፡በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው የዓለም ባንክ ባለፉት ዓመታት በንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣በትምህርት፣በጤና እና [...]