የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውል ለተጨማሪ ሶስት ወራት ተራዘመ

2021-09-16T11:15:22+00:00

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን ከመስከረም 4/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት እስከ ታህሳስ 3/2014 ዓ.ም አራዝሟል፡፡ በመዲናዋ ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ወደስራ ከገቡ በኋላ በአማካይ 3 መቶ 92 አውቶቡሶች በየቀኑ አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በሁሉም አውቶቡሶች ላይ GPS በመግጠም የክትትልና ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ይህም በቀን በአማካኝ ለ182 ሺህ ተጠቃሚዎች አገልግሎት በመስጠት የተሳፋሪ የጊዜ ቆይታን በአማካይ ከ60 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ዝቅ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡም እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ ማህበራትም በውሉ መሰረት የተቀመጡ የአሰራር ስርዓቶችን ስራ ላይ በማዋል ከዚህ የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አሳስቧል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከጥቅምት 9/2013 ዓ.ም [...]

የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውል ለተጨማሪ ሶስት ወራት ተራዘመ2021-09-16T11:15:22+00:00

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአፋር ክልል የ200 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

2021-09-16T08:57:11+00:00

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሰመራ ከተማ በመገኘት ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ ድጋፉን አስረክበዋል ። የአፋር ህዝብ የጁንታው እቅድ እንዳይሳካ እና ኢትዮጵያን ለመበታተን የሸረበው ሴራ በማክሸፍ በኩል ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳሉት አሸባሪው የህወሃት ቡድን የከፈተው ጦርነት አንድ ወይም ሁለት ክልል ላይ ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮጵያዊያን ላይ በመሆኑ በጋራ መረባረብ ይገባናል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት እንዳያብብ እና አንድነታችን ተጠብቆ ከትውልድ ወደትውልድ እንዳይሸጋገር በማድረግ እኩይ የሆነ ተግባራቸውን ማፈራረስ እና ተግባራዊ እንዳያደርጉት በማድረግ በኩል አብረን የቆምን ቢሆንም ድንበር ላይ ያላችሁት ግን በዋናነት እናንተ የአፋር ክልል ህዝቦች ችግሩን ተጋፍጣችኋል፤ እኩይ ተግባሩ [...]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአፋር ክልል የ200 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።2021-09-16T08:57:11+00:00

በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሚመራ የልዑካን ቡድን በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ገባ።

2021-09-16T08:29:55+00:00

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ፣የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ባሀብቶችን እና የንግዱን ማህበረሰብ ያካተተ ልዑካን አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ገብቷል። ሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፍሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለልዑካኑ አቀባበል አድርገዋል ።

በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሚመራ የልዑካን ቡድን በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ገባ።2021-09-16T08:29:55+00:00

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ ክልል 385 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

2021-09-15T13:58:12+00:00

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአማራ ክልል አሸባሪው የህወሓት ቡድን በፈጸመው ወረራ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለማገዝ የ350 ሚሊየን የጥሬ ብር እና የ35 ሚሊየን 134 ሺህ 128 የአይነት በጠቅላላው 385 ሚሊየን 134 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በባህርዳር ከተማ በመገኘት ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር አስረክበዋል ። አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ በከፈተው ወረራ ንጽሐን ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሷል ያሉት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ሕዝብ እና የከተማ አስተዳደሩ ከጎናችሁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ድጋፉን አበርክተናል ብለዋል። ድጋፉ ከከተማዋ የመንግስት ሰራተኞች፣የንግዱ ማህበረሰብ እና ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ መሆኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል [...]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ ክልል 385 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።2021-09-15T13:58:12+00:00

በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመራ ልዑክ ለአማራ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ባህርዳር ከተማ ገባ።

2021-09-15T13:52:01+00:00

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሰርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ መለሰ አለሙ ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ከፍተኛ አመራሮች ፣ከከተማዋ የተውጣጡ ባለሀብቶች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ለአማራ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ባህርዳር ከተማ ገብቷል። ልዑኩ ባሕር ዳር ከተማ በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል

በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመራ ልዑክ ለአማራ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ባህርዳር ከተማ ገባ።2021-09-15T13:52:01+00:00

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ አሙዲን የተስፋ ብርሃን የምግባ ማዕከል በመገኘት ማዕድ አጋሩ።

2021-09-13T07:42:49+00:00

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ጋር በመሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሱማሌ ተራ አካባቢ በሚገኘው አሙዲን የተስፋብርሐን የምገባ ማዕከል በመገኘት በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ከማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በዓልን አክብረዋል። በአዲስ አመትን በማዕከሉ የምገባ አገልግልት ተጠቃሚ ከሆኑ የህብረተሰብ ከፍሎች ጋር ተገኝተው በዓሉን በማክበሬ ደሰታ ተሰምቶኛል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉትን ዜጎች መደገፍ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆን አለበት ብለዋል። የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ላደረገው ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎቹ ስም አመስግነዋል። የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው ሚድሮክ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ [...]

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ አሙዲን የተስፋ ብርሃን የምግባ ማዕከል በመገኘት ማዕድ አጋሩ።2021-09-13T07:42:49+00:00

“በአፋር ግንባር ታሪክ ከሰሩት እና ጁንታዉን ጠራርገው ካወጡ ጀግኖች ጋር በዓልን በጋራ አክብረናል”:-ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

2021-09-13T07:36:18+00:00

ምክትል ከንቲባ ወ/ ሮ አዳነች አቤቤ እና የፌዴራል የከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በአፋር ግንባር ተገኝተው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎችን ጋር የአዲስ አመት በዓልን አሳልፈዋል። ዛሬ ከሰዓት በአፋር ግንባር ታሪክ ከሰሩት እና ጁንታዉን ጠራርገው ነፃ ባወጡት ቦታ ላይ የአዲስ አመት አቀባበል ድንቅ በሆነ የበዓል ስነ-ስርዓት ማሳለፋቸውን ምክትል ከንቲባ ወ/ ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡ በሰራዊታችን ላይ የሚታየው የሞራል ፣ የቆራጥነት እና የሀገር ወዳድነት መንፈስ ጽናት ቆዩ እንጂ ሂዱ አያሰኝም ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ክብርና ምስጋና ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እና ለመላው የፀጥታ ሀይላችን በማለት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ። በስነስርዓቱ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች ከፍተኛ [...]

“በአፋር ግንባር ታሪክ ከሰሩት እና ጁንታዉን ጠራርገው ካወጡ ጀግኖች ጋር በዓልን በጋራ አክብረናል”:-ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ2021-09-13T07:36:18+00:00

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አዲሱን አመት በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

2021-09-13T06:52:41+00:00

በውጭና በሃገር ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ውድ የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን አደረሳችሁ!!! እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳንም ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ፤ የሚሉ ቃለት አዲስነትን ማላበስ ጉልበት አላቸው፤ ተስፋን የማጋባት ኃይል አላቸው፤ ደስታን የማጎናጸፍ አቅም አላቸው፤ እንኳንም ከዘመን ዘመን አሸጋገረን አሸጋገራችሁ፡፡ ዘመን ሰው ነው ፤ ዘመን እኔና እናንተ ነን፤በዘመን ውስጥ እኛ ነን ጎልተን መታየት ያለብን፡፡ የሚጠቀስ ተግባር፣ የሚነገር ታሪክ፣ አርአያ የሚሆን ሥራ፤ በዘመኑ ውስጥ እንድንሰራ ዘመኑ ተሰቶናል፡፡ በዘመን ስሌት መጠቀም የእኛ ፋንታ ነው፡፡ መሸጋገራችን ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ የሁላችን ኃላፊነት ነው፡፡ ከዘመን ዘመን መሸጋገርን ጊዜ መቁጠር ብቻ አድርገን እንዳንወስደው፤ 2013 አልፎ 2014 ተተካ ብለን ስንል በእኛ ህይወት ውስጥ ስለተተካው አዲስ መንፈስ፣ ስለተተከለው ኢትዮጵያዊነት፣ ስለሰነቅነው አገልጋይነት፣ ስለቀጣይ ተግባራዊ [...]

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አዲሱን አመት በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት2021-09-13T06:52:41+00:00

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአዲስ አመት መቀበያ የጳጉሜ ቀናት ዛሬም በተለያዩ መርሐግብሮች በመካሄድ ላይ ይገኛል።

2021-09-10T06:53:45+00:00

በዛሬው ዕለትም የድል ቃልኪዳን ብስራት ቀንን በማስመልከት በመሐል ማዘጋጃ ቤት "አዲስ አበባ" ከበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር የአዲስ አመት ዋዜማ በዓል እየተከበረ ነው። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በወጣቶች የእንኳን አደረሳችሁ የአዲስ አመት ስጦታ ፖስት ካርድ ተሰጥተዋል ። አዲስ አበባ በባለፈው አመት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉን አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል ። በመጪው አዲስ አመትም የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት ያማከሉ እና ነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ እንደሚሰራ አቶ ጃንጥራር አመልክተዋል ። የድል ብስራት ማብሰሪያም የቢጫ ፊኛ ወደሰማይ ለቀዋል ። #ቃልእገባለሁ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአዲስ አመት መቀበያ የጳጉሜ ቀናት ዛሬም በተለያዩ መርሐግብሮች በመካሄድ ላይ ይገኛል።2021-09-10T06:53:45+00:00

2021-09-10T06:39:34+00:00

"ለኢትዮጵያ የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን" :-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳስታወቁት ድል የገቡትን ቃል በማክበር፣ለቃል ታምኖ በመሥራትና ቃልን በተግባር በመግለጥ የሚገኝ ነው ብለዋል፡፡ ቃል ማክበር ካለ የድል ብሥራት አለ፤ ለኢትዮጵያ የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን ብለዋል። መንግሥትና ህዝብ የሚኖሩት በቃል ኪዳን ነው፤ እንደ መንግሥትና እንደ ሕዝብ ለገባናቸው ቃል ኪዳኖች ታማኞች ከሆንን ሀገር ሰላም፣ ምቹና ባለጸጋ ትሆናለችም ነው ያሉት። ቃል ኪዳን የዓለም ህልውና የተመሠረተበት ሥርዓት ነው፤ ሰው ከሰው፣ ሰው ከአካባቢው፣ አካባቢ እርስ በርሱ ተጠባብቆና ተግባብቶ የሚኖረው በቃል ኪዳን ነው ብለዋል። #ቃልእገባለሁ

2021-09-10T06:39:34+00:00
Go to Top