“ሁለንተናዊ ርብርብ ለትምህርት ተቋማት ደረጃ መሻሻል!”
ALEMSTEHAY ASHINE2023-08-24T12:30:12+03:00በሚል መሪ ቃል የ2016 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጉባዔን አስጀምረናል። ጉባዔው የ2015 የትምህርት ዘመን ድክመትና ጥንካሬዎች የሚለዩበት፣ ትውልድን በዕውቀትና በስነ ምግባር የማነጽ ስራችን ያለበት ደረጃ የሚገመገምበት፣ ጥንካሬዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ድክመቶች ደግሞ መንስዔዎቻቸው ተለይተው የሚታረሙበት አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋል። በ2015 የትምህርት ዘመን ያስመዘገብናቸው የተሻሉ ውጤቶች እና ፍሬዎቻቸው ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም፣ በሰራነው እና ባሳካነው ሳንረካ ለበለጠ ድል ዝግጅት ለማድረግ ጉባዔው ጠቃሚ ሀሳቦችን እንደሚያነሳ ተስፋ አደርጋለሁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ