“ማገልገል ክብርም መታደልም ነው! ክብር ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለሚያገለግሉ” ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ALEMSTEHAY ASHINE2023-09-07T13:00:45+03:00“ማገልገል ክብርም መታደልም ነው! ክብር ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለሚያገለግሉ" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
“ማገልገል ክብርም መታደልም ነው! ክብር ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለሚያገለግሉ" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል ሆናለች፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ የአባልነት ሰርተፍኬቱን በቻይና ቤጂንግ በመገኘት ከፌደሬሽኑ አመራሮች ተቀብለዋል፡፡ የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን በ85 ሀገራት የሚገኙ 242 በላይ ከተሞችን በአባልነት ያቀፈ ተቋም መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡ ፌደሬሽኑ አባል ከተሞች በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ልምድ በመጋራት በትብብር እንዲሰሩ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡
የተለያየ ብቃት እና ችሎታ ያላቸው ወጣቶች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ያቀረቡበት ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ዛሬ ተጀምሯል። እንበርታ ፣ እንፍጠር ፣ ፈተናን ለማለፍ መፍትሔ ላይ እናተኩር። ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ
በኮልፌ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እና 5 ተገኝተን የጎበኘን ሲሆን፣ በማዕከሎቹ የቴክኖሎጂ ስራዎች፣ የአገልግሎት አከባቢን ምቹ የማድረግ፣ የነዋሪ መረጃ አያያዝ ስርዓት በቴክኖሎጂ በመደገፍ የማደራጀት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎትን የሚያቀላጥፉ ስራዎች ተሰርተዋል። የዲጂታል አገልግሎት ከተጀመረባቸው የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ የመሬት፣ የገቢዎች፣ የግንባታ ፍቃድ፣ የንግድና የጤና ዘርፎች ላይ ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠን ሲሆን ነዋሪዎቻችንን የሚመጥን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን። ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (ማስ ስፖርት) ፕሮግራም ተከናወነ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ባስተላለፉት መልዕክት ስፖርት የግል ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር ለሰላም ያለው አስተዋጽኦ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ጤናችንን እየጠበቅን የከተማችንን ሰላምና ልማት አጠናክረን መቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በቤተሰብ ደረጃ የተጀመረውን "የሌማት ትሩፋት" ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ሁለተኛ ዙር የ90ቀን ልዩ እቅድ ይፋ ማድረጉን ያስታወሱት አቶ መለሰ ይህ እቅድ ከመደበኛ ስራዎቻችን ባሻገር ለብልፅግና ጉዞ ለምናደርገው ጥረት ልማታችንን የሚያፋጥን ስለሆነ ይህንን ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በይፋ መጀመሩን አብስረዋል። በዛሬው ዕለት በተከናወነው ከተማ አቀፍ ማስ ስፖርት [...]
የወረዳውን ብሎም የአዲስ አበባ ከተማን ሰላም ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ለመጠበቅ በተደራጀው ህዝባዊ ሰራዊት ጥቆማ ከ 25 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ተያዘ። በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 6 በአንድ ሬስቶራንት ወለል ስር የመጋዘን ፍቃድ ሳይኖረውና ዘይቱን የገዛበት ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ባለመቻሉ በዛሬው ዕለት በንግድ ግብረሐይሉ ከ 25ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ተከማችቶ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል። ከ1250 ካርቶን በላይ ባለ 5 ሊትር ዘይት ጨለማን ተገን በማድረግ ከለሊቱ 8:00 አካባቢ በመጋዘን ሲያራግፍ ህዝባዊ ሰራዊቱ ሲያደርግ በነበረው ክትትል መገኘቱን ሊረጋገጥ ችሏል።
ዛሬም እንደ ትናንቱ ፈተናዎችን በድል ተሻግረን፣ እጃችንን ለምስጋና እንዘረጋለን!! የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፣ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ለችግሮች ያለመንበርከክ፣ በፈተና ሳይበገሩ የማለፍና እንቅፋቶችን ተሻግሮ ድል የማድረግ የክብር ስም ነው፡፡ ሀገራችን በታሪኳ ያለ ፈተና ያሳለፈቻቸው ዘመናት እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ በብርቱ ልጆችዋ ጥረትና በፈጣሪ ቸርነት የሚገጥማትን የችግር ውርጅብኝ እየተቋቋማች እዚህ ደርሳለች፡፡ ዛሬም የሀገራችንን ብርቱ አቅም ሊገዳደር የመከራ ዶፍ በዙሪያችን ቢያስገመግም፤ እንደ ሐምሌ ክረምት በችግር ደመናቸው ሕይወታችንን ሊያጨልሙ የሚቋምጡ ኃይሎች ቢሰበሰቡም መጓዛችንን አናቆምም፡፡ በጽኑ ማንነታችንና በፈጣሪ እገዛ ለምንታመነው እኛ ሁሌም ከክረምቱ ባሻገር የሚመጣው ብሩህ ጸደይ ጎልቶ ይታየናል፤ ከጨለማው ማዶ ደማቅ ብርሃን እንዳለ እናውቃለን፡፡ የትናንቱን ጨለማ እንዳለፍነው ሁሉ÷ የዛሬውን ጽልመት የማንሻገርበት ምክንያት እንደሌለ እያመንን፣ ብርታትና [...]
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ14ቱ ኮሌጆች በተለያየ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸው 10 ሺህ 120 ተማሪዎችን አስመረቀ :: የዕለቱ የክብር እንግዳ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጥነው ለተመረቁት ለሃገራችሁ መፃኢ እድል ተስፋ ልትሆኗት ለዛሬው ቀን በቅታችኋል እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ፈተና ሰብሮ እስካላስቀረ ድረስ ይቀርፃል ፤ ይሞርዳል በፈታኝ ሁኔታ የማለፍ ጥበብን ያስተምራል፥ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዛሬ ተመሪቂዎች በፈተና ሳትረቱ ለሃገራቸሁ ጠንክራችሁ መሰራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል። የህዝባችንን ተጠቃሚነትና የሃገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪ ፣ የፈጠራ ስራና ቴክኖሎጂን ማስፋፋት ቁልፍ መሳርያ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል:: የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በሙያ፤ በክህሎትና በአስተሳሰብ የተሻሉ ሰልጣኞችን በማፍራት አገራችን በያዘችው ወሳኝ የለውጥ ምእራፍ [...]
የከተማ አስተዳደሩ የስራ አፈጻጸምና የቀጣይ የትኩረት ነጥቦች ላይ በሚከናወነው የግምገማ መድረክ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ እና ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በተገኙበት ተጀምሯል። ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆየው የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በሚሳተፉበት የግምገማ መድረክ የ2014 ዓ.ም የመንግስትና የፓርቲ ስራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2015 ዓ.ም የትኩረት ነጥቦች ላይ ውይይት ይደረጋል። በከተማዋ ከተከናወኑ በርካታ ተግባራት መካከል በጥንካሬ ትምህርት የሚወሰድባቸውን በመለየት የማስፋት እና ቀጣይነት የማረጋገጥ ሂደት ላይ ትኩረት ተደርጎ ውይይት ይደረጋል። እዲሁም ባለፈው በጀት አመት የነበሩ እጥረቶችን እና ጉድለቶችን በመለየት የመሙላትና የእርምት መውሰድ የሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ውይይት ይከናወናል። ከዚህም በተጨማሪ የቀጣይ በጀት አመት የትኩረት የሚሹ [...]
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ያጠናቀቀውን መደበኛ ስብሰባ ተከትሎ አባላቱ የአረንጓዴ አሻራ ካኖሩ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ያለውን የአድዋ 00 ኪሎሜትር ፕሮጀክት ጎብኝተዋል። የማዕከላዊ ኮሚቴው አባላት በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳትፎ አድርገዋል። በመቀጠልም በግንባታ ላይ ያለውን የአድዋ 00 ኪሎሜትር ፕሮጀክት ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስለ ፕሮጀክቱ ዓላማ፣ ይዘትና ፋይዳ እንዲሁም አሁን ስላለበት ደረጃ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሀገራዊ የሰላምና ደህንነት፣ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማሳለፍ ውይይቱን አጠናቋል። ኢትዮጵያን [...]