የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
ራዕይ
በ2022 የአዲስ አበባ ከተማ ሰፊ የስራ ዕድልና የተሻለ ገቢ የፈጠሩ ለኢንዱስትሪ ልማት ሰፊ መሰረት የጣሉ ልማታዊ አስተሳሰብ ያዳበሩ ብቁና ተወዳዳሪ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከተስፋፋባቸው የአፍሪካ ከተሞች ቀዳሚ ሆና ማየት ፡፡
ተልዕኮ
መንግስታዊ የድጋፍ ማዕቀፎችን ተደራሽ፣ የተቀናጀና ውጤታማ በማድረግ፣ የገበያ ልምድና ተወዳዳሪነትን በማጎልበት ለስራ ዕድልና ለኢንዱስትሪ ልማቱ መሰረት የሚጥሉ ኢንተርፕራይዞችን በማስፋፋት በየደረጃው የሰለጠነና የበቃ የሰው ሃይል በማፍራት፤ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ በማቅረብና በማሸጋገር፤ ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ዜጎችን የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘዴዎችን በመጠቀም ፍትሐዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲፋጠን ማድረግ ነው፡፡
የሴክተሩ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
ዘላቂ የስራ ዕድል ፈጠራ
- የሕዝብ ተሳትፎ ልማት ማሳደግ
- የመረጃ ሽፍን ጥራትና ተደራሽነትን ማሳደግ
- አስተምሮህና ልማታዊ ኮሙኒኬሽን ሥራ ማሳደግ
- የህብረተሰብ እርካታን ማሳደግ
- የሴቶችና ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ
- የሥራ ዕድል ፈጠራን ማጎልበት
የኢንተርፕራይዝ ልማት
- የኢንተርፕራይዞች ልማት ማሳደግ
የተቋሙን የአሰራር ሂደት በኢንስፔክሽን ማረጋገጥ
- ዘመናዊ የአንድ ማዕከል በማደራጀት የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋነትና ተደራሽነትን ማሻሻል፣
- ውጤታማ የሀብት አጠቃቀም ስርዓትን ማሻሻል
- ምርጥ ተሞክሮ የመቀመርና የማስፋፋት አሰራርን ማሳደግ
- ብልሹ አሰራር አመለካከትና ተግባር መቀነስ
- የትስስር፣ የባለ-ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችና አሰራር ስርዓት ማሳደግ
ብልሹ አሰራር አመለካከትና ተግባር መቀነስ
- አደረጃጀትና አሰራርን ማሻሻል
- የክትትልና ድጋፍ አሰራርን ማሳደግ
ተቋማዊ አቅም ግንባታ እና ሽግግር ተግባራትን ማሳደግ
የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ