በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በመካሄድ ላይ ባለው የድጋፍ ሰልፍ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።
ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከኦሮሚያ ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ከተሞች የተውጣጡ በርካታ ነዋሪዎች የወጪ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልጋ ገብነት የሚቃወሙ ፣የሀገር መከላከያ ሰራዋት የድጋፍ እና የጁንታው ህውሓት ቡድንን የሽብር ተግባር የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮችን አንግበዋል።
ከኦሮሚያ ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ከተሞች የመጡ ሰልፈኞች ከ50ሺህ በላይ ፈረሶቻቸውንም በማሰለፍ ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ለመደገፍ እና አሸባሪውን የህወሀት ቡድን ለመቃወም ከማለዳው ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ታድመዋል።