አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

2023-05-16T13:24:43+03:00

በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ኮልፌ ቀራንዮ ፤በአራዳ፣በአቃቂ ቃሊቲ፤በየካ፤ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ ፣በለሚ ኩራ ፣በቂርቆስ፣በጉለሌ፣እና በልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከግንቦት 10/2015 ዓ.ም እስከ ግንቦት 23/2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቢሮ ቁጥር 101 (ለም ሆቴል አከበቢ ኤም ኤ ህንፃ ላይ) በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡ በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ማንነቱ የሚገልፅ መታወቂያ ያዞ በአካል መቅረብ ይኖርበታል፡፡በውክልና ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ [...]