open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በለውጡ የተመለሱ የአርሶ አደሩ ጥያቄዎች በቀጣይ ምላሽ በሚያገኙባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የአርሶ አደር ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በውይይቱ ሁሉን አቀፍ ፣አካታች አንዱን ጠቅሞ አንዱን የማይገፋ የሚለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በከተማችን ተከማችቶ የቆየውን የአርሶ አደሩን ጥያቄ በመመለስ እውን መሆን መጀመሩን አስረድተዋል።

አርሶአደሩ በግል፣ ተደራጅቶ እንዲሁም አቅም የሌላቸው ደግሞ ይዞታቸውን በማያጡበት አግባብ አቅም ካላቸው ጋር መስራት የሚያስችላቸው መመሪያ መውጣቱን / አዳነች ገልጸዋል።የአርሶአደር ተወካይ ኮሚቴዎች ለወከላቸው አርሶ አደር ታማኝ ሆነው ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እንዲረባረቡ እና አርሶአደሩ በስሙ የሚነግዱ ደላሎችን ሊታገላቸው እንደሚገባም / አዳነች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ /ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አርሶአደሩ ከተማ መጣብን ሳይሆን መጣልን ብሎ እንዲያስብ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያከሩጫና ከስፖርትነት ባለፈ የአብሮነት ፣የስኬት ፣የፍቅር እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን የሃገራችንን ገጽታ ገንብቷል "ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

20ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ

በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 20ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደወትሮዉ በድምቀት፣ አዝናኝ እና አስደሳች በሆነ መልክ በከተማችን እየተካሄደ ይገኛል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሩጫና ከስፖርትነት ባለፈ የአብሮነት ፣የስኬት ፣የፍቅር እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን የሃገራችንን ገጽታ ገንብቷል ብለዋል ።እኛም እንደሩጫው ሁሉ ሃገራችን በምታደርገው ድህነትን የማሸነፍ፣ ዘላቂ እድገትን የማስመዝገብ እና የታላቅነት ጉዞ በየእለት ኑሮአችን አሸናፊዎች እንሁን ሲሉ / አዳነች መልዕክት አስተላልፈዋል።