ምክትል ከንቲባው አክለውም፤ በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የተቀዛቀዘው የአገልግሎ አሰጣጥ በፍጥነት እንዲስተካከል አሳስበዋል። እንዲሁም የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ በተጠናከረ መንገድ መሰራት እንዳለበት ምክትል ከንቲባዉ በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል።
አዲሱ የከተማዋ የበላይ አመራር ከመደበኛው የክትትልና ድጋፍ አሠራር ስልት በተጨማሪ ከሚዲያዎች በሚገኙ ተጨባጭ መረጃዎች ጭምር በመታገዝ የአፈጻጸም ክትትልና የእርምት እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል፡፡
ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በመሆን ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም መሾማቸው ይታወሳል። በእለቱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔን በምክትል ከንቲባ ማእረግ መሾሙ አይዘነጋም።