በዕለቱ የሀይማኖት ተቋማት በዓል አድማቂዎች፣ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊ ማህበራት ሰብሳቢዎች፣ ማህበረ ቅዱሳን እና ሌሎች አካላት የተገኙ ሲሆን በዘመነ አዲስ ቤትን ማደስ፣ በቤተ አዲስ ፍቅርን፣ መተባበርን፣ ይቅርታን፣ አንድነትን መንገስ በሚል መሪ ቃል በአቶ ዮናስ አረጋይ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ የመነሻ ዕቅድ ሰነድ ቀርቧል፡፡ ዕቅዱም በዋናነት በአንድ ወረዳ አንድ ቤት፣ በአዲስ አመት ውብ መንደር፣ በአዲስ ዘመን ስጦታ ለሀገሬ፣ የጐዳና ላይ ትርኢት፣ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ፌስቲቫል፣ ሰብአዊ አገልግሎት ደም መለገስ የሚሉ አበይት ተግባራት የተካተቱበትን ሰነድ አቅርበዋል፡፡ ተሳታፊዎቹም በቀረበዉ ሰነድ ላይ ተጨማሪ ሀሳብ በማከል ለመስራት ዝግጁነታቸዉን ገልፀዋል፡፡
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ፣ የዓለም ዲኘሎማቶች መናኸሪያ እንደመሆኗ መጠን የበለጠ መሥራት እንደሚጠይቅና ለክልል ከተሞችና ለአፍሪካም አርአያና ሞዴል መሆን እንደሚጠበቅባት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም በአንድ ወረዳ ሶስት ወጣቶች በመምረጥ በ117ቱም ወረዳዎች የማደራጀትና የማስተባበር ሥራውን መሬት ለማውረድ ወጣቶቹ ኃላፊነታቸውን ተረክበው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡