open

አርሶአደሩ እውነትን ይዞ እያቀረባቸው ያሉ ጥያቄዎች በአጭር ጊዜያት ይፈታሉ" ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለከተማዋ አመራሮች የሥራ መመርያ ሰጡ

አርሶአደሩ እውነትን ይዞ እያቀረባቸው ያሉ ጥያቄዎች በአጭር ጊዜያት ይፈታሉ" ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በለውጡ የተመለሱ የአርሶ አደሩ ጥያቄዎች በቀጣይ ምላሽ በሚያገኙባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የአርሶ አደር ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በውይይቱ ሁሉን አቀፍ ፣አካታች አንዱን ጠቅሞ አንዱን የማይገፋ የሚለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በከተማችን ተከማችቶ የቆየውን የአርሶ አደሩን ጥያቄ በመመለስ እውን መሆን መጀመሩን አስረድተዋል።

አርሶአደሩ በግል፣ ተደራጅቶ እንዲሁም አቅም የሌላቸው ደግሞ ይዞታቸውን በማያጡበት አግባብ አቅም ካላቸው ጋር መስራት የሚያስችላቸው መመሪያ መውጣቱን / አዳነች ገልጸዋል።የአርሶአደር ተወካይ ኮሚቴዎች ለወከላቸው አርሶ አደር ታማኝ ሆነው ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እንዲረባረቡ እና አርሶአደሩ በስሙ የሚነግዱ ደላሎችን ሊታገላቸው እንደሚገባም / አዳነች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ /ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አርሶአደሩ ከተማ መጣብን ሳይሆን መጣልን ብሎ እንዲያስብ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

 

በቀጣይም የሚወጡ ህጎችና መመሪያወች ለአርሶአደሩ የሚኖራቸው ፋይዳ ታሳቢ ይደረጋል ያሉት አቶ መለሰ የከተማውን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ አመራሩ አቅሙን አሟጦ እንደሚጠቀም ነዋሪው እንዲረባረብ ጠይቀዋል።በውይይቱ የተሳተፉ አርሶ አደሮች በበኩላቸው አዲስ አበባ በእጥፍ እንድትሰፋ እና እንድታድግ ያለንን ሁሉ ሰጥተን ተገቢውን ክብር እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ሳናገኝ እና ስንበደል ቆይተን የበደሉን ወድቀው በማየታችን አስደስቶናል ብለዋል።በጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጠቃሚ መሆን በመጀመራቸው እና ትኩረት በማግኘታቸው የከተማ አስተዳደሩን ያመሰገኑት አርሶአደሮቹ በአካባቢያችን በርካታ የመሰረተ ልማት ችግሮች ትኩረት ይሰጥልን ብለዋል፡፡"የተቀናጀ የለውጥ አመራር ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የአርሶ አደር ተወካዮች ጋር በተካሄደው ውይይት ከምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ፣የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ /ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ ፣የክፍለ ከተሞች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

 

Read 13 times