ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።በተጨማሪም የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡ ሲሆን በሰመዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል
የፕሮጀክቱ አካል የሆነ እና ለትራፊክ ፍሰት እንዲሁም ለሰላም እና ጸጥታ ስራ የሚያግዙ 17 ፓትሮል ተሸከርካሪዎችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል፡፡በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ ተሸከርካሪዎቹን አስረክበዋል፡፡በመርሃ ግብሩ በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ እንደገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል አለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነድፎ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡