open

አስተዳደር

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Februarie 2020

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ 84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።በተጨማሪም የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡ ሲሆን በሰመዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል

የፕሮጀክቱ አካል የሆነ እና ለትራፊክ ፍሰት እንዲሁም ለሰላም እና ጸጥታ ስራ የሚያግዙ 17 ፓትሮል ተሸከርካሪዎችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል፡፡በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ ተሸከርካሪዎቹን አስረክበዋል፡፡በመርሃ ግብሩ በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ እንደገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል አለም ባንክ 200 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነድፎ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር / / ጌታሁን መኩሪያ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ /ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ መምህራን ጋር ውይይት አካሂደዋል ።ከመምህራን ጋር በተደረገው ውይይት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በሁሉም አቅጣጫዎች ከለውጡ መነሻ አንስቶ እዚህ እንዲደርስ ካደረጉት አካላት አንዱ አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰብ ነው ብለዋል ።ኢትዮጵያ ባለፉት 2 አመታት የጀመረችው ለውጥ ትኩረት የሀገረ መንግስት ግንባታ ነው ያሉት / አዳነች ይችን ሀገር ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር ሁሉም የራሱን አሻራ ሊያሳርፍ እንደሚገባ ተናግረዋል

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸው 2039 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል ።በምረቃው ስነስርዓት ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ፣የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋልበ ምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ለተማሪዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በዩንቨርስቲ ቆይታችሁ ያሳለፋችኋቸው የደስታና የመከፋት ፤መውደቅና መነሳቶች ከመደበኛ ትምህርታችሁ ጎን ለጎን ችግርን የመጋፈጥ የህይወት ልምምድ ፣የመተሳስብ እና የመተባበር አቅም ያገኛችሁበት ሆኖ እንዳለፈ አምናለሁ ብለዋል ።የኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲን ጨምሮ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች በቀሰማችሁት የእውቀት ብርሃን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማንንም ሳይጠብቁ በመላው ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ የሀገርን ሰላም በመጠበቅ እና በሀቀኝነት ህዝብን በማገልገል በተግባር መለወጥ እንደሚገባ / አዳነች አቤቤ ገልጸዋል