open

ማህበረሰብ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Mei 2020

የአካል ጉዳተኞች ተሽከርካሪዎቹ ኢንተርናሽናል ፈንድ ፎር አፍሪካ በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስተባባሪነት ከዊልተር ፎር አፍሪካ የተሰጠ ሲሆን ለበዓል የሚሆን የበግ ስጦታም ለአካል ጉዳተኞቹ አበርክተዋል።

 ወይዘሮ አዳነች ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተዳረጉ አካል ጉዳተኞችን መደገፍ እና መንከባከብ የሁላችንም የዘወትር ተግባር ሊሆን ይገባል ያሉ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩም አካል ጉዳተኞች ያለባቸውን ማህበራዊ እና ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ጽኅፈት ቤት ሃላፊ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አቶ ኤፍሬም አለሙ የተባሉ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ ጽኅፈት ቤት ሃላፊ ለተገልጋይ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

 

ጉያ የተባለ አገር በቀል የማኑፋክተሪንግ ካምፓኒ ከሚያመርታቸው ሜዲካል ማስኮች በሽያጭ ከሚያገኘው ትርፍ 1% በአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ምገባ የሚሆን የአንድ አመት ድጋፍ ስምምነት አድርጓል፡፡የድጋፍ ስምምነቱን በአዲስ አበባ ከተማ የማህበራዊ ትረሥት ፈንድ ሃላፊ / ፍቅርተ ነጋሽ እና የጉያ ማኑፋክቸሪንግ ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙባረክ ከማል ተፈራርመዋል፡፡

 

የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ የሚከናወን የማህበራዊ ድጋፍና የአብሮነት ንቅናቄ በተለያዩ ዝግጅቶች ከፊታችን ጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 በከተማችን አዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ንቅናቄው በዋነኛነት

✔የተጀመረውን የፍቅርና የአብሮነት ጉዞ ለማጠናከር

✔አዲሱን ዓመት በተስፋ ለመቀበልና እንኳን አደረሳችሁ ለመባባል

✔የከተማ አስተዳደሩ ለሚያከናውናቸው ተግባራት የነዋሪዎችን ተሳተፎ ለማሳደግ

✔በጎ ፈቃደኝነትንና የመረዳዳትን ባህል ለማሳደግ

✔ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ጋር ይበልጥ አብሮ ለመስራት የሚያስችል መደላደል ለመፍጠርና የከተማዋን ገጽታ ለመገንባት ይሆናል፡፡