open

መሰረተ ልማት

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/መሰረተ ልማት/ዘመናዊ አውቶቢሶች

 

/ ታከለ ኡማ በሚኖሩበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት / ቀነኒ ሁንዴ መኖሪያ ቤት በመገኘት የቤት እድሳት መርሀግብሩን አስጀምረዋል።በየአካባቢው የሚገኙ ለኑሮ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አቅመደካማዎች መኖሪያ ቤታቸው የሚታደስ ይሆናል።

 

በከተማ አቀፍ ደረጃ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ ስራ ተጀመረ፡፡መርሃግብሩን በይፋ ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ እና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ እንደገለጹት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ኢትዮጵያውያን ከድህነት ለመላቀቅ የምታደርገውን ትግል እውን ማድረጊያ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡የግድቡ ትርጉም ከኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ባለፈ የኢትዮጵያውያን የክብር እና የመተባበር ተምሳሌት ጭምር በመሆኑ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ግድቡ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ ከዚህ ቀደም ያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ ጥሪያቸው አቅርበዋል፡፡

 

መንገዱ አዲስ አበባና አምቦ መስመርን የሚያገናኝ ነው።

መንገዱ የአዲስ አበባ መውጪያዎችን ከኦሮሚያ አጎራባች ከተማዎች የሚያገናኙ መንገዶችን የመገንባት አንዱ ክፍል ነው።የሀይሌ ጋርመንትጀሞ መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን በቀጣይም ሁለተኛው ምእራፍ ግንባታ የሚቀጥል ይሆናል።

 

300 አውቶብሶችን ማቆም የሚችለውና ዘመናዊ የጥገናና የተለያዩ አገልግሎቶችን ያካተተው የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመርቀ።የአውቶብስ ዴፖውን መርቀው ስራ ያስጀመሩት / ታከለ ኡማ ናቸው።

ዴፖው ከመሬት በታች የሚገኝ የአውቶብስ ማቆሚያን ያካተተ ነው።
የቃሊቲ አውቶብስ ዴፖ ዘመናዊ ጋራዥ፣ዘመናዊ ነዳጅ ማደያዎችን፣የአውቶቡሶችን ውጭ አካል ቀለም መቀባት የሚችል እንዲሁም አንድን አውቶብስ ከሁለት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ማጠብ የሚችል መሳሪያ ተገጥሞለታል።