open

Items filtered by date: Desember 2019

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Desember 2019
Items filtered by date: Desember 2019

 

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ሓላፊ / ዮሃንስ ጫላ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ኢንሹራንስን በሁሉም የከተማዋ ወረዳዎች ለማዳረስ እየተደረገ ባለው ዝግጅት ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰተዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ወረዳዎች ከአንድ ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚ ለማድረግ ከጥቅምት ወር ጀምሮ የቤት ለቤት ምዝገባ እየተካሔደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አማካኝነት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የጤና ተቋማት የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ፣የመድሃኒት አቅርቦት እና ሌሎች አስፋላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ሓለፊው ተናግረዋል፡፡

Published in ማህበረሰብ

 

/ ታከለ ኡማ በመጪው ሳምንት ጎተራ አካባቢ ግንባታው የሚጀመረውን እና አፋር መንደር የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮጀክት ላይ ያለውን ዝግጅት ተመልክተዋል። የአፋር ተወላጅ በሆኑ ባለሀብቶች በጎተራ አካባቢ የሚገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የግል ይዞታቸው በሆነ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ነው።መኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንቶችንና አገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ያካተተ ነው።

ከዚህ ቀደም በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በቻይና ኩባንያዎች የሚገነቡ ሁለት ግዙፍ የመኖሪያ መንደሮች ይፉ መደረጋቸው ይታወቃል።

Published in መሰረተ ልማት

 

 

በአራት ቢሊዮን ብር በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ከተማዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በቀን 600 ሊትር የምግብ ዘይት የሚያመርት ፋብሪካ ግንባታው ተጀመረ፡፡500 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህል አቀነባብሮ 600 ሊትር የምግብ ዘይት የሚያመርት የዘይት ፋብሪካ ግንባታው ተጀምሯል።የሸገር የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ የተጀመረው ቦሌ ክፍለከተማ የተባበሩት አደባባይ አከባቢ ነው፡፡የሸገር የምግብ ዘይት ፋብሪካ ግንባታ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / ታከለ ኡማን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ / ጫልቱ ሳኒ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሚድሮክ ኢትዮጵያ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች በተገኙበት ግንባታው ተጀምሯል፡፡በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት / ታከለ ኡማ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ይዞ የቆየውን ቦታ ለከተማዋ ሁሉን አቀፍ ልማት እንዲውል በማድረጋቸው በከተማው ነዋሪ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Published in መሰረተ ልማት

 

በአዲስ አበባ ከተማ በመንግስት ትምህርት ቤት ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሞዲስ እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ ለማቅረብ የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።በዚሁ መሰረት የፊታችን ታህሳስ 26 ቀን 2012. በሚሊኔየም አዳራሽ የቁሳቁሶቹን ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን አስተባባሪዎቹ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ 700ሺህ ሞዴስ እና 200ሺህ የሴቶች ፓንት ለማሰባሰብ እቅድ መያዙን የተገለጸ ሲሆን በመርሃ ግብሩም 20ሺህ በላይ በጎ ፍቃደኞች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።በተጨማሪም በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ የሲ.ኤን.ኤን የአመቱ ጀግና ተብላ የተሸለመቺውን ፍሬወይኒ መብረሃቱ የክብር አቀባበል እንደሚደረግላት ተገልጿል።

Published in ማህበረሰብ

 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / ታከለ ኡማን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የዳቦ ማምረቻ የግንባታ ሂደት ምልከታ አድርገዋል።በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ ለማምረት ከስድስት ወራት በፊት ግንባታው የተጀመረው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ የግንባታ ስራን በፍጥነት ለማጠናቀቅ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ተጥቶ እየሰራ ይገኛል።በከተማዋ የሚታየውን የዳቦ አቅርቦት ችግር የሚያቃልል እና የዋጋ ንረቱንም በተጨባጭ መልኩ እንደሚያረጋጋ የሚጠበቀው ይህ ግዙፍ የዳቦ ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡

Published in ማህበረሰብ
Maandag, 23 Desember 2019 07:55

ETRSS- 01

 

የሳተላይቷ ጠቅላላ ከሸብደት 72 ኪሎ ግራም ሲሆን ነገ ታሕሳስ 10/2012 ከማለዳው 12 ሰዓት 21 ደቂቃ ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡
ሳተላይቷ በተወነጨፈች በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የህዋ ጥግ ላይ የምሕዋር ቦታዋን ትይዛለች፡፡

በኢትዮጵያ ቻይና መንግስት በጀት የተገነባችው የመረጃና ኮሙኒኬሽን ሳተላይት የምትመጥቀው ከቻይና የጠፈር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው።

ሳተላይቷ ለግብር፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመገናኛና ቴክኖሎጂ ለመሳሰሉት አገልግሎት መረጃ ለመስጠት ነው፡፡

Published in መሰረተ ልማት

 

 

The 50 Best Places to Travel in 2020:-Addis Ababa , Ethiopia

በዓለም ላይ ታዋቂ የጉዞ መረጃ አውጪ ድህረገፅ የሆነው ትራቨል ኤንድ ሌይዠር በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር 2020 ሊጎበኙ ከሚገባቸው 50 የዓለማችን ስፍራዎች ውስጥ አዲስ አበባ ከተማን በቀዳሚነት አስፍሯታል።በቅርቡ የዘንድሮውን የሰላም ኖቤል ሽልማትን የተቀበሉት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቤተመንግስት አስገንብተው ለህዝብ ክፍት ያደረጉትን የአንድነት ፓርክ የከተማዋን አዲስ ገፅታ መሆኑን ድህረገፁ አስነብቧል።

Published in ቱሪዝም

በቻይና በተካሄደው የዓለም የዩንቨርስቲዎች እግር ኳስ ውድድር አፍሪካን በመወከል ተሳታፊ ለነበረው የኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩንቨርስቲ ልዑካን አቀባበል ተደረገላቸው።ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና አዘጋጅነት በተካሄደው የዓለም የዩንቨርሲቲዎች እግር ኳስ ውድድር አፍሪካን በመወከል ለተሳተፈው የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩንቨርሲቲ እግር ኳስ ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የዕውቅናና ምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል

Published in ልዮ ልዮ

 

 

/ ታከለ ኡማ በቅርቡ ከተቋቋመው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላት እና አመራሮች ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ኮሚሽኑ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የውሳኔ ሃሳብ የምክረ ሃሳብ እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለሚመለከታቸው አካላት የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ አባላቶቹ ተናግረዋል፡፡

Published in ማህበረሰብ

 

 

ለረዥም ዓመታት የንግድ ትርዒትና ኤግዚቢሽን የማዘጋጀት አገልግሎት እየሰጠ በሚገኘው የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል 22 ሄክታር መሬት ላይ ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶችን በማሳተፍ የፓን አፍሪካ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል የምክክር መድረክ / ታከለ ኡማ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡300 በላይ የሚሆኑ በልዩ ልዩ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አኢትዮጵያውያን ባለሃብቶችን በታደሙበት የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት / ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባን አለምዓቀፍ ከተማነትን የመጠነ ሁሉንም የንግድ ዘርፎች የያዘ ትልቅ የንግድና የኢንቨስትመንት መንደር የመገንባት ውጥን እንዳለው ገልፀዋል፡፡

Published in መሰረተ ልማት