open

Items filtered by date: Januarie 2020

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Januarie 2020
Items filtered by date: Januarie 2020

 

23 በተለያዩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ የቦርድ አባላትም ተመርጠዋል።
የተማሪዎች የምገባ ኤጀንሲ የቦርድ አባላት ሆነው የተመረጡት--

1. / አለምጸሃይ ጳውሎስ - ሰብሳቢ
2.
/ የፍሬዓለም ሽባባው - /ሰብሳቢ
3.
/ አምለሰት ሙጬ
4.
አቶ ስኩር ካርዲን
5.
አቶ አበበ ባልቻ
6.
/ በድሉ ዋቅጂራ
7.
/ ሮማን ታፈሰወርቅ
8.
አቶ ጥላሁን ጉግሳ
9.
አቶ ያሬድ ሹመቴ
10.
አቶ አማን ፍሰሃጽዮን
11.
አቶ ፍትህ ቶላ
12.
/ ፍሬህይወት /ህይወት

Published in አስተዳደር

 

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቀ፡፡

 

በዚህም መሠረት

1. / እንዳወቅ አብጤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ

2. / ሰናይት ዳምጠው የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
3.
/ ነጂባ ሐክመል የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
4.
አቶ ሺሰማ /ስላሴ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
5.
አቶ አብዱልቃድር መሃመድ የአቃቤ ህግ ቢሮ ኃላፊ
6.
/ ኤፍራ አሊ የባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
7.
አቶ ሐይሉ ሉሌ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
8.
አቶ ዘላለም ሙላት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
9.
/ ደመላሽ ከበደ የኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
10.
አቶ ስጦታው አከለ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
11.
አቶ ነጋሽ ባጫ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ
12.
አቶ ይመር ከበደ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ
13.
አቶ ሙሉጌታ ተፈራ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
14.
አቶ አብዱልፈታ ዩሱፍ የንግድ ቢሮ ኃላፊ
15.
አቶ አዱኛ ደበላ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ
16.
አቶ አብርሃም ታደሠ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ

Published in አስተዳደር

 

 

/ ታከለ ኡማ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገውን የፈረንሳይ ፓረክ ጎብኝተዋል፡፡

 

እድሳት እየተደረገላቸው የሚገኙት በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ የመዝናኛ ፓርኮች ለህዝብ ክፍት እንደዲሆኑ ተወሰነ።

 

ፓርኮቹ ለአገልግሎት በሚመችና መሰረተልማት ባሟላ መልኩ እድሳት እየተደረገላቸው ሲሆን ጎን ለጎንም ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ነው የተወሰነው።ማንኛውም ነዋሪም በመዝናኛ ፓርኮቹ ያለክፍያ መጠቀም ይችላል።

Published in ማህበረሰብ

በህብር ወደ ብልጽግና" አዲስ አበባ ከተማ አቀፍ የሴቶች መድረክ / / ዐብይ አህመድ በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነዉ።

Published in አስተዳደር

2880 በላይ ታዳጊዎች 18 የስፖርት አይነቶች ወደ ፕሮጀክት ስልጠና ማስገባቱን የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት_ኮሚሽን 2012 . የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ልማት መርሃግብር 122 የስልጠና ጣቢያ በሴቶች እና ወንዶች 2880 በላይ ታዳጊዎች ወደ ፕሮጀክት ስልጠና በይፋ አስገብቷል፡፡
የታዳጊ_ወጣቶች ስልጠና ዘመናዊ እና ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አሰራርን በተከተለ መልኩ የሚሰጠ ሲሆን ለስልጠናው 124 አሰልጣኞች ዝግጁ ሆነዋል፡፡

Published in አስተዳደር

 

/ ታከለ ኡማ በግንባታ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ አልሚ ድርጅቶች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት በከተማዋ ውስጥ የተጀመሩ ህንጻዎች እንዲጠናቀቁ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ሰጪ ቡድን እንደሚያቋቁም ቃል በገቡት መሠረት በዛሬው ዕለት ድጋፍ ሰጪ ቡድኑን አደራጅተዋል፡፡

 

በዚህም መሠረት በከንቲባ /ቤት የሚመራ ከመሬት አስተዳደር ከግንባታ ፈቃድ ከመንገድ ባለስልጣን ከፕላን ኮሚሽን ከኮንስትራክሽን ቢሮ እንዲሁም ከመሠረተ ልማት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተውጣጣ ቡድን በዛሬው ዕለት ተቋቁሟል፡፡

Published in መሰረተ ልማት

 

/ ታከለ ኡማ ከሐይሌ ጋርመንት አደባባይ - ጀሞ 3 አደባባይ 4.5 / ከማሠልጠኛ/ቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ አደባባይ 11 / ከቃሊቲ - ቂሊንጦ 11 / ከቦሌ ቡልቡላ - 40/60- ኖቫ ሪልስቴት 8.2 / እንዲሁም ከቦሌ ሚካኤል - ቦሌ ቡልቡላ 5 / ርዝመት ያላቸው መንገዶች ግንባታቸው ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

Published in መሰረተ ልማት

 

 

/ ታከለ ኡማ በግንባታው ዘርፍ የሚስተዋለውን የግንባታ መጓተትና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ዉይይት ከዘርፉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር አድርገዋል

በዉይይት መድረኩ ላይ በሶስት ክፍለከተሞች ማለትም በቦሌ አራዳ እና ቂሪቆስ ክፍለከተማ በሚገኙ 17 የሚሆኑ የተለያዩ ግንባታዎች ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ቀርቧል፡፡የዉይይቱ ተሳታፊዎች የባንክ ብድር አቅርቦትን ጨምሮ ከሊዝ አዋጅና መመሪያ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር እንዲሁም ሌሎች ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮችን በዋናነት አንስተዋል።ግንባታዎቹ የከተማው አንጡራ ሀብት ናቸዉ ያሉት / ታከለ ኡማ በግንባታው ዘርፍ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

Published in አስተዳደር

 

/ ታከለ ኡማ የትራፊክ ክፍያን በዘመናዊ መንገድ ለመቀየር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከዘርፉ ባለሞያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡የትራፊክ ክፍያዎች "ለሁሉ" አገልግሎት ከተቋረጠ በኃላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ይህም አሽከርካርዎች እንዲጉላሉ እና ረዥም ወረፋ እንዲጠብቁ ምክንያት ሆኗል፡፡ይሄን አሰራር በዘመናዊ መንገድ ለመቀየርም የከተማ አስተዳደሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

Published in ማህበረሰብ

 

 

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የከተማችን ነዋሪዎች፣ የክርስትና እምነት ተከታዮች

 

እንኳን ለገና በአል በሰላም አደረሳችሁ!

 

ገና ክፉውን የምንጠላበት፣ መልካሙን የምንመርጥበት፣ ተስፋችን የምናድስበት እና እምናታችንን የምናፀናበት ትልቅ የምልክት ቀን ነው።ገና ትልቅ ስጦታ የተሰጠበት፣ ትልቅ ፍቅር የተገለጠበት ቀን ነው።እኛም ያበበችና የበለፀገች አዲስ አበባን ለትውልድ ሰርቶ ለማስረከብ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን እና ዕውቀታችንን ሳንቆጥብ እንሰጣለን።

 

በድጋሜ መልካም የገና በአል
እወዳችዋለሁ።

 

Published in አስተዳደር