open

Items filtered by date: Oktober 2020

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Oktober 2020
Items filtered by date: Oktober 2020

"መምህራን በስነምግባር የታነጸ ፣ሀገርን መውደድ እና መለወጥ የሚችል ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መስራት አለባቸው "ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ"መምህራን በቀውስ ውስጥ ይመራሉ መጪውንም ይተነብያሉ!" በሚል መሪ ቃል አምስተኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን ቀን የምስጋና እና የዕውቅና መርሐግብር ተካሂዷል።በመርሐግብሩ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለፁት ትምህርት የእድገት ሁሉ መሠረት ነው፤ በእድገትም ሆነ በቴክኖሎጂ አደጉ የምንላቸው አገራት መሠረታቸው ትምህርት ነው ብለዋል

መምህራን እስከዛሬ ላደረጉት አስተዋፅኦ መመስገን እና ማበረታታት እንደሚገባ የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን አስፈላጊውን ትኩረት ይሰጣል ብለዋል

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ 1 ሺህ 495ኛውን የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓልን (መውሊድ) ምክንያት በማድረግ ኑሯቸውን ጎዳና ያደረጉ ዜጎችን ምሳ አበሉ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ 1 ሺህ 495ኛውን የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓልን (መውሊድ) ምክንያት በማድረግ ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ዜጎችን በዛሬው ዕለት ምሳ አብልተዋል፡፡

Published in አስተዳደር

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ዘንድሮ " አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ ብርሃን!!! " በሚል ንቅናቄ ህብረተሰቡ በአብሮነት ያለውን በማካፈል እንዲሣተፍ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሣል።ከዚህም በዋናነት ለተማሪዎች ብሩህ ተስፋ ማሣየት አንዱ ሲሆን አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ምገባ የዩኒፎርምና የትምህርት ግባትን ከሟሟላት ጎን ለጎን "አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ " በሚል ላቀረቡት ጥሪ ባንኮች በመቀበል ላደረጉት ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል

የድጋፍ ዝርዝሩ እንደሚከተለው ይገለፃል።

Published in አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ / አዳነች አበቤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በማህበር የተደራጁ ወጣቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ የብልጽግና ፓርቲ /ቤት ኃላፊ አቶ መለስ ዓለሙ እና ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መኮንን አምባዬ ጋር በመሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 9 በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው በችግኝ ተከላ፣ክብካቤና በፅዳትና ውበት ስራ ላይ ተሠማርተው አካባቢያቸውን ፅዱና ውብ ያደረጉ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር /ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በዳግማዊ ሚንሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት በመገኘት ትምህርት በይፋ አስጀምረዋል ።ተማሪዎች ከጤና ባለሙያዎች እና መምህራን የሚሰጣቸውን ምክር እና አቅጣጫ በአግባቡ እንዲተገብሩ አሳስበዋል ።የከተማ አስተዳደሩ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲሳካ ከዩኒፎርም ጀምሮ የመማሪያ ቁሣቁሶች እንዲሁም የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንደሚቀርብ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።ተማሪዎች በትምህርት ክፍለ ጊዜያቸው ከኮቪድ -19 በተጨማሪ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስተጓጐል ከሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም አካላት እንዲርቁ ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል

Published in አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች፣የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ስራ አስኪያጆች እና ሰራተኞች፣ የአራዳ ፣የየካ እና የጉለሌ /ከተሞች አመራሮችና ባለሞያዎች የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል በተጨማሪም የመንገድ ላይ ፅዳት ሰራተኞች ፣በአካባቢው የሚኖሩ በሴፍቲኔት ፕሮግራም የታቀፉ ነዋሪዎች እንዲሁም በጃንሜዳ የአትክልት ነጋዴዎች በጋራ በመሆን የጃንሜዳ አትክልት ተራን የማፅዳት ስራ ተሳትፈዋል

 

Published in አስተዳደር
Maandag, 26 Oktober 2020 11:35

አንድ ሆነን እንነሳ

አንድ ሆነን ከተነሳን የሚበግረን ምድራዊ ሀይል እንደሌለ ታሪክ ምስክር ነው”-ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችንን ግብ ከማድረስ የሚያግደን አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለም ብለዋል፡፡ኢትዮጵያዊያን አንድ ሆንን እንቁም ያሉት ምክትል ከንቲባዋ አንድ ሆነን ከተነሳን የሚበግረን ምድራዊ ሀይል እንደሌለ ታሪክ ምስክር ነውም ብለዋል::

Published in አስተዳደር

አቶ ጃንጥራር አባይ ቅጥርን በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ሁለት ቋንቋዎችን መቻል እንደግዴታ አስቀምጧል እየተባለ የሚናፈሰው መረጃዎች ከእውነት የራቀ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል፡፡

አቶ ጃንጥራር አባይ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ከሰሞኑ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በከተማ አስተዳደሩ የሰራተኞች ቅጥርን በተመለከተ ሁለት የሀገር ውስጥ ቋንቋ መቻል ግዴታ እንደሆነ ተደርጎ የተዘገበው መረጃ ትክክል አይደለም ብለዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ ለመቀጠር ሁለት ቋንቋ እንደግዴታ ነው እየተባለ የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል፡፡

Published in አስተዳደር

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ፣ባለሀብቶች እና በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦች ለተማሪዎች የሚሆን 2.5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ የከተማ አስተዳደሩን ጥሪ በመቀበልም በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ፣ባለሀብቶች እና በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦች ለተማሪዎች የሚሆን 2.5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል

በዚሁ መሠረት:-

1. የአዲስ አበባ ካቶሊክ ቤተክርሥቲያን 2 ባለ 10,ሺህ ሊትር የሚይዝ የውሃ መጠራቀሚያ ሮቶ

2. ታርጌት ሳሙና ባለ 5 ሊትር 3 ደርዘን የእጅ ሳሙና እንዲሁም ባለ 5ዐዐ ሚሊሊትር 3 ደርዘን የእጅ ሳሙና

3.ሻለቃ አትሌት ሀይሌ /ሥላሤ 400ሺህ ብር

4.የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሠራተኞች 500 ሺህ ብር

Published in አስተዳደር

በጠቅላላው 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ አስረክበዋል፡፡

በርክክቡ ወቅት ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ለወገኖቻችን አብሮነታችንን ፣ፍቅራችንን እና አጋርነታችንን መግለጻችን ሁልጊዜ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ነው ብለዋል፡፡እኛ ለኛ ካልሆንን ከሌላ ከየትም ሊመጣን አይችልም ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ወደፊትም በክልሉ ካሉ ህዝቦች ጋር ከባህል ትስስር ጀምሮ በእህትማማችነት እና ወንድማማችነት የተጀመረው ትስስር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።በአዲስ አበባና አርባ ምንጭ ከተሞች መካከል እህትማማችነት ለመመስረትና በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ አካባቢ የጋሞ ባህል ማዕከል እየተገነባ መሆኑን አዳነች አቤቤ ጠቁመዋል

Published in አስተዳደር