open

Items filtered by date: November 2020

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: November 2020
Items filtered by date: November 2020

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ አክሲዮን ማህበሩ ለሰራዊቱ ያደረገውን ድጋፍ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የቅርስ ጥበቃና ሙዚየም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴል ጄነራል ደሳለኝ ደቼ አስረክበዋል፡፡ህብረተሰቡ ለሰራዊቱ እያደረገ ያለው የሞራል ፣የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፎች ሰላም እንዲሰፍን እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ምን ያክል ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ መሆኑን ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡የከተማዋ ነዋሪዎች ሰራዊቱ በጁንታው የህውሃት የጥፋት ቡድን ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እያደረጉት ያለው ድጋፍ አበረታች መሆንን የገለጹት / አዳነች ከድል በኃላም ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ከሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ፣የአዲሰ አበባ ምክር ቤት አፈጉባዔ / ዘርፈሽዋል ንጉሴ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት አፈጉባኤ አቶ ታደለ ተረፈ ፣የአሶሳ ከተማ ከንቲባ ኡመር መሀመድ እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች 15ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዘቦች በዓል ችቦ በጋራ በመያዝ ከኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በቸርችል ጎዳና እስከ ማዘጋጃ ቤት በእግር ጉዞ በማክበር ላይ ናቸው

Published in አስተዳደር

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎቹ ያደረጉትን ድጋፍ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ተወክለው ለተገኙት ጀነራሎች አስረክበዋል ።የአራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጁንታው ህወሓት የጥፋት ቡድን ላይ እየወሰደ ያላውን የህግ ማስከበር እርምጃ ለመደገፍ ለሰራዊቱ የሚሆን ሰንጋዎችን ጨምሮ የጥሬ ገንዘብ እናጨልዩ ልዩ ቁሳቁሶች በጠቅላላው 70 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ያሉ አዲስ እና ነባር የገበያ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በጀሞ ፣በኮልፌ ፣በሃይሌ ጋርመንት እና በሌሎች አካባቢዎች በግንባታ ላይ ያሉ የአትክልት ገበያ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ከኢትዮጲያ መብራት ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ / አሸብር ባልቻ እና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጫን ጎብኝተዋል፡፡የሀይል ማመንጫው አልፎ አልፎ የሚያጋጥመውን የግብዓት አቅርቦት እና የበጀት ችግር መቅረፍ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ከስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጫ 32 ሄክታር መሬት ላይ በአመት 185 ጌጋ ዋት ሀወር የኤሌትሪክ ሀይል የሚያመነጭ ሲሆን አሁን ላይ የገቢ አቅሙ ገና በመሆኑ ምክንያት የግብዓትና የበጀት ችግር እንደገጠመው የተቋሙ ስራ አስኪያጅ / ብሩክ ኤባ ገልፀዋል።ከዚሁ ጋር ተያይዞም ምክትል ከንቲባዋ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታን የጎበኙ ሲሆን በውስጡ ያሉ ሰራተኞችን በገጠማቸው ችግሮች ዙሪያ አነጋግረዋቸዋል፡፡

Published in አስተዳደር

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች እና አርሶአደሮች ህግን እያስከበረ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት 88 ሰንጋ በሬዎችን ጨምሮ የተለያዩ በቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ።የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚሆን 8 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገብዘብ ፣ዋጋችው 12 ሚሊዮን ብር የሚሆን 88 ሰንጋ፣ 84 በግና ፍየል፣ የወር ደምዎዝ እና ሌሎች ድጋፎችን ጨምሮ በድምሩ 75 ሚሊዮን ብር በጥሬ እና በአይነት ድጋፍ አድርገዋል ።ከነዋሪዎቹ የተበረከተውን የበሬ እና ሌሎች ስጦታዎችን ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ጀነራሎች ተረክበዋል

Published in አስተዳደር

በድጋፍ መርሐ ግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ / ዘርፈሽዋል ንጉሴ፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ /ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ለዛሬ ማክሰኞ ህዳር 8 ከቀኑ 5:30 ጀምሮ እንዲካሄድ ቀን ለተቆረጠለት የድጋፍ ጥሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን በያሉበት በመሆን አጋርነታቸውን ይገልጻሉ ተብሏል፡፡በአሁኑ ሰአት የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም አጋርታቸውን ለመግለጽ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ታድመዋል፡፡

Published in አስተዳደር

በውይይቱ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ የፌደራል መንግስት በህውሃት አጥፊ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ህግን ለማስከበር በመሆኑ ዘላቂ ሰላምን ለማስጠበቅ ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል::ፅንፈኛው ቡድን ህዝቡን ሽፋን በማድረግ የራሱን ጥቅም ሲያሳድድ መኖሩን እና ጥፋቶችን ሲያቀነባብር መቆየቱን የገለጹት / አዳነች ችግሩ እዚህ ደረጃ እንዳይደርስ የፌደራል መንግስቱ ከመጀመሪያ ጀምሮ በውይይት ለመፍታት ሰፊ ጥረት ማደረጉን ተናግረዋል ከምንም በላይ ከፊታችን ያለው ጊዜ የአንድነት ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ በከተማዋ የሚገኙ የትግራይ ክልል ተወላጆች ከመላው ኢትዮጵያዊያን እህት ወንድሞቹ ጋር በመሆን ለከተማዋ ዘላቂ ሰላምና እድገት በጋራ መስራት አለበት ብለዋል።የፌዴራል መንግስት በህወሃት ጁንታ ላይ የህግ ማስከበር ስራ በትግራይ ህዝብ ላይ የተለየ ጭቆና እንደ ተፈጸመ ተደርጎ ለሚናፈሰው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጥ ለእውነት በመቆም የጥፋት ሀይሉን ተግባር ማውገዝ ይገባዋል ብለዋል

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት የጥፋት እና ክህደት የፈጸመብንን የህውኃት ቡድንን በመፋለም የኢትዮጵያችን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ውድ ህይወቱን መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ላለው መከላከያ ሰራዊታችን ደማችነን በመለገስ አጋርነታችንን በተግባር ማሳየት አለብን ብለዋል ።በህወሃት ጁንታ ወንጀለኛ ቡድን አመራሮች ላይ የተጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻን በድል እየተወጣ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ የአጎራባች ክልሎች ልዩ ሃይል እና የሚልሻ አባላት የላቀ ድጋፍ እና ክብር መስጠት ይገባል ብለዋል በዘመቻው ተሳትፎ በማድረግ ላይ የመከላከያ ሰራዊታችን፣ የአጎራባች ክልሎች ልዩ ሃይል እና የሚልሻ አባላት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን / አዳነች ገልጸዋል

Published in አስተዳደር

 

 

 

የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት አገልግሎት ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ ተካሂዷል።በጉባኤው ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት የወሳኝ ኩነት አገልግሎት ምዝገባ ማካሄድ ሙስናና የማጭበርበር ስራዎችን ለመከላከል ፣ለማህበራዊ ደህንነት አጠቃላይ የከተማዋን አገልግሎት ፍጥነት እና በትክክለኛው መረጃ ላይ ተሞርክዞ ውሣኔዎችን ለመስጠት እንዲሁም ስራዎችን በአግባቡ ለመከወን አስፈላጊ ነው ብለዋል ።የምዝገባ አገልግሎቱ በሁሉም ወረዳዎች በሚፈለገው መንገድ የተቀላጠፈ እና ዘመናዊ አገልግሎት እንዲሰጥ የከተማ አስተዳደሩ ከግብዓት ጀምሮ አስፈላጊው ነገር እንደሚሟላ / አዳነች ተናግረዋል ።የምክር ቤቱ መቋቋምም መረጃዎችን በማጥራት ተደራሽ የማድረግ ከዛም በሚገኘው ውጤት ስራዎችን ቀልጣፋ እና ፍትሃዊ መሆን እንዲችሉ ለማስቻል ስለሆነ ከምክር ቤቱ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት በተግባር ማሳየት ይኖርበታል ብለዋል።

Published in አስተዳደር