open

Items filtered by date: Desember 2020

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Januarie 2021
Items filtered by date: Desember 2020

 

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ የኔትወርክ፣ የሴኪዩሪቲ፣ የኢንተርኔትና ዋይፋይ፣ የአይፒ ቢኤክስ፣ የወረፋ ማስጠበቂያ ሲስተም፣ የዳታ ሴንተር የከተማ አቀፍ ሜይል ሲስተም ሌሎች መሰል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ስራ አስጀምረዋል ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የምንገኝበት ወቅት አለም በቴክኖሎጂ አንድ የሆነበት በመሆኑ በከተማችንም ደህንነቱ እና ጥራቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂ ማበልጸግ እና መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል አገልግሎት መስጫ የዲጂታል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ተግባራዊ መሆን አገልግሎት ፈላጊውን አካል የጊዜ፣ የጉልበት እና እንግልት ከማስቀረቱም ባለፈ ሙስናን እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከታተል ፋይዳው የጎላ መሆኑን ምክትል ከንቲባ / አዳነች ተናግረዋል

Published in አስተዳደር

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደመቀ መኮንን እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ሚኒስትሮችን ጨምሮ፣የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የተለያዩ የስፖርት ፌዴሬሽን አመራሮች በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል፡፡

Published in አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጪው 10 ዓመት የከተማዋን ዘላቂ ልማት እና እድገት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ዙሪያ 10 ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ከሁሉም የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በውይይት መድረኩ ላይ ከተማ አስተዳደሩ የሀገራችንን የብልፅግና ትልም ዕውን ለማድረግ ከወጣው ዕቅድ የተቀዳ 10 አመት መነሻ ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።መዳረሻ ዕቅዱ የተሟላ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች ፍላጎት ያካተተ እንዲሆንም በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በማድረግ ጠቃሚ ግብአት ማሰባሰብ አስፈላጊ መሆኑንም አቶ ጃንጥራር ጠቅሰዋል።

Published in አስተዳደር

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ የግል ድርጅቶች ባለቤት የሆኑ ባለሃብቶች "ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት 390 ሚሊየን ብር ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በተገኙበት አስረክበዋል፡፡በመርሃግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በዚህ ሃገር አቀፍ የልማት አጀንዳ ቃል ገብተው በተግባርም ለተሳተፉት ባለሃብቶች "ሁሌ ስንጠራችሁ የማናጣችሁ ለሀገርና ለትውልድ ለሚተርፍ መልካምነት እና ቸርነት የምትተጉ" በማለት በራሳቸውና በግል ድርጅቶች የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Published in አስተዳደር

 

የአዲስ አበባ ከተማ /ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር ሊዮ ዩሺ እና ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በአዲስ አበባ ስለሚገነቡት የአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክቶች እና ተያያዥ የትብብር ስራዎች ዙርያ ተወያይተዋል።በውይይታቸው በአዲስ አበባ ስለሚገነቡት የአፍሪካ መንደር ፕሮጀክት እና የሲ.. አፍሪካ ዋና መስሪያ ቤት እውን የማድረግ የትብብር አቅጣጫ ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

Published in አስተዳደር

የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን መሰረት 1 እስከ 4 ክፍል ባሉ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የመማሩ ማስተማሩ ሂደት በመከናወን ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡የኮቪድ19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ በተለያዩ ምዕራፎች የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን በጠበቀ መንገድ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦምብ የሶስት የጎዳና ተዳዳሪዎች ህይወት በማለፉ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ተኩል አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ቦምቡ ፈንድቶ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፡፡

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱህ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እንዲሁም የተለያዩ ሀጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጃንሜዳ የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራን ጎብኝተዋል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱህ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የከተማ አስተዳደሩ ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል እንዲደርስ ቃል በገባው መሰረት እዚህ ደረጃ ደርሶ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል ።ጃንሜዳ ለበዓሉ ማክበሪያ ዝግጁ ለማድረግ ከምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ላደረጉት ትብብር በቤተክርስቲያኗ እና በህዝበ ክርስቲያኒቱ ስም አቡነ ማቲያስ ምስጋና አቅርበዋል

Published in አስተዳደር
Maandag, 14 Desember 2020 08:24

ሰኞ ማታ ይጠብቁ

 

በአዲስ አበባ ከተማ መሬት እና መሬት ነከ የሆኑ ጉዳዮችን አሰመልክቶ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም ሰኞ ምሽት በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ /አዲስቲቪ / እና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ስለሚተላለፍ መላው የከተማችን ነዋሪዎች በተጠቀሰው ሰዓት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን!

Published in አስተዳደር

በጃንሜዳ ውስጥ ያሉ አትክልት ነጋዴዎች ከጥቂት ቀናት በኃላ ወደ ተዘጋጀላቸው የአትክልት መሸጫ ስፍራዎች እንደሚዘዋወሩ / አዳነች ተናግረዋል ።ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ዝግጁ ለማድረግ እና ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ በተከታታይ የማጽዳት ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል ሸማቹን እና አምራቹን አንድ ላይ ማገናኘት የሚያስችሉ የአትክልት እና መሰል መገበያያ ስፍራዎች በየክፍለ ከተማው ተደራሽ የማድረግ ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ / አዳነች ጠቁመዋል፡፡

Published in አስተዳደር