open

Items filtered by date: Februarie 2020

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Februarie 2020
Items filtered by date: Februarie 2020

 

/ ታከለ ከፑሽኪን አደባባይ እስከ ጎተራ እየተገነባ ያለው መንገድ የጎበኙ ሲሆን መንገዱ የዲዛይን ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የዋሻ ቁፋሮ ስራው እየተሰራ ይገኛል።መንገዱ 3.8 . ርዝመት የሚኖረው ሲሆን በሁለት በኩል 320 ሜትር ርዝመት ያለው ዋሻ(Tunnel) እና ተጨማሪ የፈጣን አውቶብስ መተላለፊያ (Bus Rapid Transit) ይኖረዋል።

 

የፑሽኪን አደባባይ ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መስከረም ወር መጨረሻ ላይ የተጀመረ ሲሆን፥ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Published in መሰረተ ልማት

 

 

በአዲሱ ማሻሻያም ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት 1-3 ሰአት እንዲሁም ከሰዓት 10:30-12:00 ውጪ ባሉ ሰዓቶች እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።ማሻሻያው የተደረገው የተለያዩ ተቋማት በሰዓት ገደቡ ምክኒያት በተለይም የግንባታ ስራዎቻቸውን ለማከናወን መቸገራቸውን ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።

በመሆኑም የትራፊክ እንቅስቃሴውን ጫና ውስጥ በማይከት መልኩ ማሻሻያው ተደርጓል።

 

እስካሁን በነበረው ህግ በከተማዋ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው።

 

Published in ልዮ ልዮ

 

 

መንገዶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል በአዲስ አበባ የሚገኙ አስሩም ክፍለከተማ ሰራ አስፈጻሚዎችና የከተማዋ የመንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎች ከኢ/ ታከለ ኡማ ጋር በከተማዋ እየገነቡ የሚገኙ መንገዶች ያሉበትን ደረጃ ገምግመዋል።

በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ጨምሮ 100 በላይ መንገዶች ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል።

 በግምገማውም የመንገዶቹ ግንባታ ያሉበት ያሉበት ደረጃ ገለፃ ተደርጓል።

Published in መሰረተ ልማት

 

 

/ ታከለ ኡማ የአድዋ 0:00 . ፕሮጀክት ፣አንድ መኪኖችን የማስቆም አቅም ያለው የታላቁ ቤተ-መንግስት የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም በአንድ ጊዜ 10 ሰው በላይ ማስተናገድ የሚችለውን ግዙፉ የቤተ-መፅሐፍት ግንባታ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

 3 እና 4 ወራት በፊት የተጀመሩት ፕሮጀክቶቹ ስራቸው በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።ፕሮጀክቶቹ ይጠናቀቃሉ ከተባሉበት ጊዜ ቀድመው እንዲጠናቀቁ እየተሰራ ይገኛል።በከተማዋ የአድዋ ድል ማስታወሻ ከሆነው ፕሮጀክት በተጨማሪ የተለያዩ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች እየተገነቡ ይገኛሉ።

Published in መሰረተ ልማት

 

በስልጠናው መክፈቻ ላይ / ታከለ ኡማ ተገኝተዋል፡፡
/ ታከለ ለሰልጣኝ አመራሮች ባስተላለፉት መልእክት አመራሩ ህዝብን ለማገልገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛና ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

Published in አስተዳደር

 

ጉለሌ እጽዋት ማእከል፣ በአካባቢው ውስጥ የሚገኘው አረንጓዴ ስፍራ እንዲሁም እንጦጦ የሚገኘው አረንጓዴ ስፍራ በአንድ ላይ የሚያስተዳድር ተቋም እንዲመሰረት ተወሰነ።ቦታዎቹ ለነዋሪዎች ማረፊያና ለቱሪዝም አገልግሎት እንዲውሉና ይህም በተቀናጀ መልኩ ለመምራት ለማስቻል ነው ተቋሙ የሚመሰረተው።ኢ/ ታከለ ኡማ በእንጦጦ እየተሰራ ያለውን የማስዋብ ስራና የቱሪዝም መስህብ ግንባታ ተመልክተዋል።ኢ/ ታከለ በተጨማሪም ከሽሮ ሜዳቁስቋም እየተገነባ ያለውን 2 . ርዝመት ያለው መንገድ ጎብኝተዋል።የመንገዱ ግንባታ ተጓትቶ ነዋሪዎች ቅሬታ እያቀረቡበት ሲሆን መንገዱ በሁለት ወር ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግም / ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

Published in መሰረተ ልማት

የክፍያ መንገዶች ስራ በቅርቡ በተመረጡ መንገዶች ይጀመራል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / ታከለ ኡማ የማዕከሉ መገንባት በከተማዋ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅን በማቅለልና የትራንስፖርት ዘርፉን በዘመነ መልኩ በመምራት በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።"አዲስ አበባ በሁሉም ነገር ሞዴል ትሆናለች ስንል የሰው ልጆችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን የትራፊክ አደጋን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በመቆጣጠር የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት በመፍጠርና ምቹ የመኖሪያ አከባቢን በመፍጠርም ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል፡፡ማዕከሉ የትራፊክ ፍሰቱን ከአንድ ማዕከል ለመቆጣጠር የሚረዱ መረጃዎች የሚያዙበትና የሚተነተኑበትም እንዲሁም ዘመናዊ ስክሪን የተገጠመላቸው መቆጣጠሪያና የትራፊክ ትግበራ ዕቅድ ማውጫ ክፍሎችን ያካተተ ነው።በአጠቃላይ ማዕከሉ 835 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን 18 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እና የከተማዋ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል ተብሏል፡፡በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ በተመረጡ ቦታዎች የክፍያ መንገዶች ስራ እንደሚጀምሩም / ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

Published in መሰረተ ልማት

ባለፉት ስድስት ወራት 1383 በላይ የህዝብ ቅሬታዎች ለጽህፈት ቤቱ ቀርበው መፍትሄ አግኝተዋል፡፡
በከተማዋ የተጀመሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት 2012 በጀት ዓመት 6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም የበላይ አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር ገምግሟል፡፡ በግምገማ መድረኩ የጽህፈት ቤቱ ሓላፊ / አለምፅሐይ ጳውሎስ በከተማዋ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች ተግባራዊ ተደርገው አመርቂ ውጤቶች መመዝገቡን ገልፀዋል ፡፡
በተለይ በትምህርት ቤቶች ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን መፍጠር የተማሪዎች ምገባ፣የተማሪዎች የደንብ ልብስ እና የመማሪያ ቁሳቁስ አቅርቦት እና ሌሎች ስራዎችን በዘላቂነት ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ሴክተር ተቋማት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ሓላፊዋ ተናግረዋል፡፡

Published in አስተዳደር

 

በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እስከ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ምስል መለየት የሚያስችሉ የደህንነት ካሜራዎችን ለመግጠም እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በዘርፉ ልምድ ካለው ድርጅት ጋር በአዲስ አበባ ከተማ ቴክኖሎጂውን መዘርጋት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ጀማል በከር የዜጎችን ደህንነት በቴክኖሎጂ ለማስጠበቅ ትኩረት እየተሰራ ሲሆን ቴክኖሎጂው ዜጎች ከደህንነት ስጋት ተላቀው የእለት ተእለት ተግባራቸውን እንዲከውኑ ያግዛል ብለዋል፡፡

Published in መሰረተ ልማት

በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውይይት እየተደረገ ነው።በውይይቱ ላይ ሚንስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።በመድረኩ ግድቡን አስመልክቶ በመደረግ ላይ ስላሉት ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

Published in አስተዳደር