በከተማዋ ወጣቶችና በጎ ፈቃደኞች የተቋቋመው ኮሚቴ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የንጽህና እቃዎችን የማሰባሰብ ስራውን ዛሬ በይፋ ጀምሯል፡፡
ህብረተሰቡም ከነገ ጀምሮ ወደ መስቀል አደባባይ በመምጣት ማንኛውንም የንጽህና እቃ መለገስ
ይችላሉ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ መግዛት ለማይችሉ ወገኖች ህብረተሰቡ አቅሙ በፈቀደው ልክ ድጋፍ በማድረግ የቫይረሱን ስርጭት እንግታ ሲል
ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
25 አምቡላንሶች ለጤና ጣቢያዎች እና ስድስቱ ደግሞ ለሆስፒታሎች ተከፋፈለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ እና የከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ የአምቡላንሶቹን ቁልፍ ለተወካዮች አስረክበዋል፡፡
ተቋቋመ።የትራንስፖርት ዘርፉን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር ምክክር አድርገዋል።
የከተማዋን የትራንስፖርት ችግርን በተመለከተ የመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርብ የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴም ተቋቁሟል።ኮሚቴው በከተማዋ ያሉ የትራንስፖርት አማራጮችና አስተዳደራዊ ሁኔታዎች ላይ ጥናት የሚያደርግ የመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርብ ይሆናል
ኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ተገኝቷል" በሚል ከወጣው መረጃ በኋላ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን የሚቆጣጠር ግብረሀይል ተቋቋመ።በከተማዋ የንግድ ቢሮ የሚመራው ግብረሀይሉ ከነገ ጠዋት ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ የፍራፍሬ ችግኝ ተከሉ፡፡የዓለም የምግብ ፕሮግራም 2050 እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 70በመቶ የምግብ አቅርቦት በከተማ ግብርና እንዲሸፈን ፕሮጀክት ቀርፆ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
የከተማ ግብርና ማደግ የጤናም የኢኮኖሚም ፋይዳ ያለው መሆኑን የገለጹት ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠርም የከተማ ግብርናን ማሳደግ አንዱ መንገዳችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማም ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዛሬው ዕለት በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የፖም /አፕል/ ፍራፍሬ ችግኝ ተክለዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ለነዋሪው ተጨማሪ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡በከተማዋ ውስጥ የከብት እርባታን ጨምሮ በፍራፍሬ ምርት ፣ ንብ ማነብ እንዲሁም አትክልትን በማምረት ስራ ላይ ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣቶችን እና እናቶችን በማደራጀት ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ የከተማው የወንዝ ዳርቻ ልማት አካል የሆነው የከተማ ግብርና ነዋሪው የተጎዳ አከባቢን መልሶ እንዲያገግም ከማድረግ በተጨማሪ የራስ የምግብ ፍጆታን በመሸፈን ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡
በዋነኛነት በቀጣይ የአዲስ አበባ ከተማ ታክሲ ተራ አስከባሪዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተቀራርበው በሚሰሩባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡የታክሲ ተራ አስከባሪዎቹ በትራንስፖርት አሰጣጥ ላይ ፣ በታሪፍና ስምሪት ፣ ባለው የፓርኪንግ ችግር እንዲሁም ሌሎች በስራ ቦታ በሚያጋጥሟቸው የህግ ማስከበር ችግሮች ዙሪያ ጥያቄያቸውን ለኢ/ር ታከለ ኡማ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ ፣ የደም ልገሳ በማድረግ ፣ በክረምት ችግኝ በመትከል ፣ በጽዳት ዘመቻ ላይ በመሳተፍ እንዲሁም የአከባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ረገድ የታክሲ ተራ አስከባሪዎቹ እያደረጉት ላለው ተሳትፎ ኢ/ር ታከለ ኡማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ኢ/ር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል።
ኢ/ር ታከለ ነዋሪዎችን የምናገለግልበት ስሜትና ተግባር እስካሁን ከነበረው ሊጨምር ይገባል ብለዋል።
አዲሱ የከተማ አስተዳደር ወደ ኃላፊነት ከመጣ በኋላ የነዋሪዎችን ጥያቄ ሊመልስና የከተማዋን ደረጃ ሊመጥን በሚችል መልኩ እርምጃዎች ቢወሰዱም ፍጥነቱ ግን ሊጨምር ይገባል ብለዋል።
ይህን ማሳካትም በተለያዩ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ አመራሮች ተግባርና መመዘኛ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ ከዚህ የህዝብ ፍላጎትና ከከተማ ከአስተዳደሩ ትልም ጋር መራመድ የማይችሉ አመራሮች ከእንግዲህ ቦታ እንደማይኖራቸውም ኢ/ር ታከለ ገልጸዋል።
የሸገር ዳቦን ፋብሪካ ኢ/ር ታከለ ኡማ ፋብሪካው ያለበት ደረጃን ተመልክተዋል።
ከወራት በፊት ግንባታው የተጀመረው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሲቪል ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የማሽን ተከላው እየተከናወነ ይገኛል።
የማምረቻ ማሽን ተከላው በውጪ ባለሙያዎች እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ማሽኑ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ያማሏ ዘመናዊ ማሽን ነው።ፋብሪካው የሚያስፈልገውን ሀይል ማቅረብ የሚችል ትራንስፎርመር በግዢ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከቀናት በኋላ ይጠናቀቃል።ከዳቦ ፋብሪካው ግንባታ ጎን ለጎንም የዱቄት ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ የማሽን ተከላ ላይ ይገኛል።
ዳቦ ፋብሪካው ከቅርብ ጊዜ በኋላ ስራውን የሚጀምር ሲሆን ምርቱን በየክፍለ—ከተማዎች የሚያሰራጩ ተሽከርካሪዎችም ተዘጋጅተዋል።የዳቦ ምርቱን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ወጣቶች የተደራጁ ሲሆን ለመሸጫ የሚሆኑ አራት መቶ ከአገልግሎት ውጪ የነበሩ አንበሳ የከተማ አውቶብሶች ዝግጁ ተደርገዋል።
ሲምፖዚየሙ “የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌትነት ለሃገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ይገኛል።የጋሞ ልማት ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ባዘጋጀው ሲምፖዚየም የጋሞ ተወላጆች፣ ወዳጆች እና የልማቱ ደጋፊዎችን ጨምሮ ከ25 ሺህ በላይ ታዳሚዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።