ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት
– ከ1997- 2007 ግብር ዘመን ውዝፍ እዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች እዳው በምህረት ቀሪ እንዲሆን
– ከ2008 - 2011 ግብር ዘመን እዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ቅጣትና ወለድ ተነሥቶ ፍሬ ግብር በቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
ካቢኔው በተጨማሪም ቤታቸው ለተቀመጡ ሠራተኞች ደሞዝ ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ግለሠቦች እንዲሁም ለተከራዮቻቸው የኪራይ ቅናሽ ላደረጉ አከራዮች የታክስ ጫና ማቃለያ ውሣኔዎች አሥተላልፎአል፡፡
በከተማ አቀፍ ደረጃ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ ስራ ተጀመረ፡፡መርሃግብሩን በይፋ ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ እና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ እንደገለጹት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ኢትዮጵያውያን ከድህነት ለመላቀቅ የምታደርገውን ትግል እውን ማድረጊያ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡የግድቡ ትርጉም ከኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ባለፈ የኢትዮጵያውያን የክብር እና የመተባበር ተምሳሌት ጭምር በመሆኑ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ግድቡ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ ከዚህ ቀደም ያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ ጥሪያቸው አቅርበዋል፡፡
መንገዱ አዲስ አበባና አምቦ መስመርን የሚያገናኝ ነው።
መንገዱ የአዲስ አበባ መውጪያዎችን ከኦሮሚያ አጎራባች ከተማዎች የሚያገናኙ መንገዶችን የመገንባት አንዱ ክፍል ነው።የሀይሌ ጋርመንት —ጀሞ መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን በቀጣይም ሁለተኛው ምእራፍ ግንባታ የሚቀጥል ይሆናል።
300 አውቶብሶችን ማቆም የሚችለውና ዘመናዊ የጥገናና የተለያዩ አገልግሎቶችን ያካተተው የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመርቀ።የአውቶብስ ዴፖውን መርቀው ስራ ያስጀመሩት ኢ/ር ታከለ ኡማ ናቸው።
ዴፖው ከመሬት በታች የሚገኝ የአውቶብስ ማቆሚያን ያካተተ ነው።
የቃሊቲ አውቶብስ ዴፖ ዘመናዊ ጋራዥ፣ዘመናዊ ነዳጅ ማደያዎችን፣የአውቶቡሶችን ውጭ አካል ቀለም መቀባት የሚችል እንዲሁም አንድን አውቶብስ ከሁለት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ማጠብ የሚችል መሳሪያ ተገጥሞለታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ለሚገኙ አርሶአደሮች ከ200 በላይ የውሀ ፓምፖችና 5 ትራክተሮች አበርክቷል።የውሀ ፓምፖቹና ትራክተሮቹን ያበረከቱት ኢ/ር ታከለ ኡማና የአዲስ አበባ የብልፅግና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ናቸው።የከተማ አስተዳደሩ ካበረከተው የትራክተር ስጦታ በተጨማሪ የተለያዩ ባለሀብቶች የትራክትር ስጦታ አበርክተዋል።ስጦታውን ለአርሶ አደሮቹ ያበረከቱት ኢ/ር ታከለ ኡማ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እናደርጋታለን ስንል ለሁሉም የተመቸች ከተማ እናደርጋታለን ማለታችን ነው፤ይህ እቅድም አርሶአደሮቻችን ያካተተ እንጂ የገፋ አይሆንም ብለዋል።
የአዲስ አበባ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዘመን ጆነዲን እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠበት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጠረው የግንዛቤ ስራ የከተማዋ ነዋሪዎችን የአንድነት ስሜት ይበልጥ ከመፍጠሩ ባለፈ የይቻላል መንፈስን ያጠናከረ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡የግድቡ ግንባታ ከተበሰረበት ጀምሮ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ስለአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ከ3 ሚሊዮን 6 መቶ ሀምሳ ሺ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በንቅናቄ ስራዎች ማሳተፍ መቻሉን አቶ ዘመን ገልጸዋል፡፡
በሰአት እስከ 30 ሺህ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግደው ተርሚናሉ ከቀላል ባቡር አገልግሎትና ከፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ጋር የተሳሰረ መሆኑ ነው የተገለጸው።የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና የመንገደኞች መተላለፊያ ድልድይ እንዲሁም ባለ ስምንት ወለል ህንፃም ያካተተ ነው ።የተርሚናሉ ግንባታ በተለይ በአካባቢውን የሚታየውን መጨናነቅ በመቀነስ በኩልና የህዝብ ትራንስፖርትን በማዘመን በኩል የጎላ ድርሻ ይኖረዋልም ተብሏል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ የከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ዛሬ ማለዳ ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡
ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ እና የትራንስፖርት ቢሮ ፣ የትራፊክ ማኔጅመንት እና የትራንስፖርት ስምሪት ሃላፊዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና አጠቃቀም ላይ የወጡ ክልከላዎችን እና ገደቦች አተገባበርን በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ቃኝተዋል፡፡
በምልከታቸውም በመንግስት እና በግል የትራንስፖርት አቅራቢዎች በተለይም በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓታት ላይ የአውቶቡስ እና የታክሲዎች የምልልስ ሂደት የሚፈለገውን ያክል አለመሆን እና ረጃጅም ሰልፎች እንዳሉ አስተባባሪው ታዝበዋል።
ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የሰላም ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በኃይማኖት አባቶች የታወጀው ሀገራዊ የፀሎት ማጠናቀቂያ መርሃግብር ላይ ተገኝተዋል ።የፀሎት መርሀግብሩ ለአንድ ወር መቆየቱ ይታወቃል።
ባለፈው አንድ ወር ታውጆ የነበረው የፀሎት መርሃግብር የኮሮና ቫይረስ በአለምና በሀገራችን መከሰትን ተከትሎ ነው።