open

Items filtered by date: Augustus 2020

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Augustus 2020
Items filtered by date: Augustus 2020

1. አቶ መለሰ አለሙ

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ /ቤት ኃላፊ

2. አቶ ኤፍሬም ግዛው

በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ /ቤት ኃላፊ

3. ወይዘሮ አልፍያ ዩሱፍ

በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ /ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

Published in አስተዳደር

ጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የተወያየ ሲሆን በከተማዋ የሚታየውን የመኖሪያ ቤትና የትራንስፖርት ችግር ከመፍታት አንፃር አፅንኦት ሠጥቶ ተወያይቷል።በከተማችን ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር እና በከተማዋ እየታየ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ካቢኔው በተለያዩ አማራጮች ሃሳቦች ዙሪያ ሠፊ ውይይት አድርጎ ውሳኔውን አስተላልፏል።

በዚሁ መሰረት -

Published in አስተዳደር

"አዲስ አበባ የበጎ ፍቃድ ማዕከል እንድትሆን ወጣቶች ፣የኪነጥበብ እና የስፖርቱ ማህበረሰብ የሚያደርጉት ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል!"-ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እና በምክትል ከንቲባ ደረጃ የመንግስት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ከስፖርት ማህበረሰብ አባላት እና ከመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በውይይቱ እንደገለጹት በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘው 2012 / ወጣቶች ፣የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣የስፖርቱ ማህበረሰብ እና መላው ነዋሪ ከተማችን እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ እንድትሆን ዘርፈ ብዙ ጥረት አድርገዋል ብለዋል።

Published in አስተዳደር

 

ጉያ የተባለ አገር በቀል የማኑፋክተሪንግ ካምፓኒ ከሚያመርታቸው ሜዲካል ማስኮች በሽያጭ ከሚያገኘው ትርፍ 1% በአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ምገባ የሚሆን የአንድ አመት ድጋፍ ስምምነት አድርጓል፡፡የድጋፍ ስምምነቱን በአዲስ አበባ ከተማ የማህበራዊ ትረሥት ፈንድ ሃላፊ / ፍቅርተ ነጋሽ እና የጉያ ማኑፋክቸሪንግ ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙባረክ ከማል ተፈራርመዋል፡፡

Published in ማህበረሰብ

 

የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ የሚከናወን የማህበራዊ ድጋፍና የአብሮነት ንቅናቄ በተለያዩ ዝግጅቶች ከፊታችን ጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 በከተማችን አዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ንቅናቄው በዋነኛነት

✔የተጀመረውን የፍቅርና የአብሮነት ጉዞ ለማጠናከር

✔አዲሱን ዓመት በተስፋ ለመቀበልና እንኳን አደረሳችሁ ለመባባል

✔የከተማ አስተዳደሩ ለሚያከናውናቸው ተግባራት የነዋሪዎችን ተሳተፎ ለማሳደግ

✔በጎ ፈቃደኝነትንና የመረዳዳትን ባህል ለማሳደግ

✔ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ጋር ይበልጥ አብሮ ለመስራት የሚያስችል መደላደል ለመፍጠርና የከተማዋን ገጽታ ለመገንባት ይሆናል፡፡

Published in ማህበረሰብ

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የከተማዋ የንግድ ማህበረሰብ በተማሪዎች ምገባ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን በማገዝ፣ በገበታ ለሸገር እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ለነበራቸው ንቁ ተሳትፎ ወይዘሮ አዳነች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡መጪውን አዲስ ዓመት ስንቀበል በአብሮነትና በመረዳዳት ስሜት መሆን ይኖርበታል ያሉት ወይዘሮ አዳነች ለዚህም የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

241 ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች መመገቢያና ማብሰያ አዳራሽ ግንባታ፣ ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ስርጭት፣ ለአንድ ተማሪ አንድ ጫማ መርሃ-ግብር (600 ተማሪ) የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት (400 ተማሪ) እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤት ለሚማሩ 600 ተማሪዎች የደንብ ልብስ ለማዘጋጀት የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

Published in አስተዳደር

ምክር ቤቱ በከተማችን ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን፣ የሚከሰቱ ግጭቶችና አለመግባባቶችን ቀድሞ ለመከላከል፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የነዋሪውን የሰላም ባለቤትነት ለማረጋገጥ የተቋቋመ ነው፡፡

በምስረታ ጉባኤው ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የኃይማኖት አባቶች ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡የምክር ቤት ማቋቋሚያ መርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የበርካታ ዓለምአቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ የምክር ቤቱ መሠረታዊ ተግባር ነው ብለዋል፡፡የሰላሟ ጠንቅ የሆኑ የምሽት ቅሚያን ጨምሮ የተሽከርካሪ ስርቆት በቡድን በመደራጀት የህብረተሰቡን ሰላም የማደፍረስ እና ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የነዋሪውን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ ወይዘሮ አዳነች አሳስበዋል፡፡

Published in አስተዳደር

በአዲስ አበባ ከመሬት ጋር ተያይዞ በሚነሱ ችግሮች እና ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን አስቀድሞ ለመከላከል ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር እየተሰሩ ባሉ ህግን የማስከበር ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡በከተማችን እየተስፋፋ ያለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን እና ህገ-ወጥ ግንባታን ለመከላከል እና አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ መንስዔውንና የመፍትሄ ሃሳብን የሚጠቁም መመሪያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠንቶ እንዲቀርብ አቅጣጫ ሰጥተዋል ወይዘሮ አዳነች።

Published in አስተዳደር

 

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ከመንገድ እና ትራንስፖርት እንዲሁም አሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ዘርፍ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በከተማዋ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ላይ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ረጃጅም ስልፎች ቀስ በቀስ መቀነስ ይገባል ብለዋል፡፡ለዚህም የብዙኃን ትራንስፖርት አቅርቦትን በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻል ባለፈ የስምሪት ስርዓቱን የማዘምን ስራዎች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ / አዳነች አቤቤ ጠቁመዋል፡፡

በቅርቡ ይፋ የተደረገውን ፈጣን የአውቶቡስ መስመር (BRT) ፕሮጀክትን በፍጥነት በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑን ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

 

Published in አስተዳደር

 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንስራ የሸክላ ማዕከልን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በማዕከሉ ውስጥ በሸክላ ስራ የተሰማሩ የዘርፉ ሙያተኞችን አበረታተዋል፡፡

የተለያየ የእጅ ሙያ ክህሎት ያላቸውን ሴቶች በማደራጀት እና የገበያ ትስስር በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደረግም / አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡--- ስንል ሸክላውን ሳይሆን የሚታይና የሚዳሰስ እና ለትውልድ የሚሻገር ስራን እንስራ ማለት ነው ያሉት / አዳነች ዘርፉን በዘመናዊ መንገድ በማደራጀት ሙያተኞቹን እንደሚደግፉም ገልጸዋል፡፡

Published in አስተዳደር