open

Items filtered by date: September 2020

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: September 2020
Items filtered by date: September 2020

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና የወቅቱ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል በውስን ሰው እንዲከበር መወሰናቸውን አባገዳዎቹ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡም እራሱን እና ቤተሰቡን ከኮቪድ 19 በመጠበቅ በአባ ገዳዎች ህብረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በዓሉን እንዲያከብር አባገዳዎቹ አሳስበዋል፡፡

የኢሬቻ በዓል የሰላም የፍቅር እና የምስጋና በዓል ነው ያሉት አባ ገዳዎቹ መላው የኦሮሞ ወጣት በዓሉን ከፖለቲካ በጸዳ መንገድ እንዲያከብር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Published in አስተዳደር

ኑር ሱልጣን መሀመድ /ቴገም የምግብ ኮምፕሌክስ/"አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ" በአምስት ሚሊየን ብር 12ሺህ 500 ጫማ መግዛት የሚያስችል ገንዘብ ለምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ አስረክበዋል፡፡ነገ መልካም ትውልድ ለማፍራት ዛሬ የምንዘራው ዘር ወሳኝ ነው ያሉት / አዳነች ጥሩ ትውልድ ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የተለያዩ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ማህበራዊ ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፤

ኑር ሱልጣን መሀመድ የቴገም የምግብ ኮምፕሌክስ ባለቤት፤ እኔም ልጆችን ማስተማር ይመለከተኛል ብለው ከአዳማ ድረስ መጥተው ድጋፍ በማድረጋቸው በከተማ አስተዳደሩ እና በተማሪዎቹ ስም ምክትል ከንቲባዋ አመስግነዋል፡፡

Published in አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በልማት ሳቢያ ተነሺ የሆኑ አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም በተዘረጋው አሰራርና አደረጃጀት ዙሪያ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የአርሶ አደር ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት በተለያዩ ጊዜያት በልማት ሳቢያ በርካታ አርሶ አደሮች ለማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ችግሮች ተዳርገዋል ብለዋል፡፡ከቀያተቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን እና የአርሶ አደር ልጆችን በተገቢው መንገድ በማጣራት በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመፍጠር የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደረግ / አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡አርሶ አደሩን ሽፋን በማድረግ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በምንም ሁኔታ ተቀባይነት የለውም ያሉት ምክትል ከንቲባዋ በአርሶ አደር እና በአርሶ አደር ልጆች ስም መሬት የሚዘርፉ ደላሎች እና ህገወጦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡

Published in አስተዳደር

 

በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም ይገባል" ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም በመጠናቀቁ እና የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል አከባበር ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ምክትል ከንቲባ አዳነች የመስቀል ደመራ በአል በሰላም እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ የሀይማኖት አባቶች ፣ምእመናን እና ፀጥታ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ባስቀመጠው የሰው ቁጥር መሰረት የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ ክብረ በዓል በመስቀል ደመራ በአል ዕለት በታየው የአብሮነት እና የትብብር መንፈስ በሰላማዊ መንገድ መከበር ይኖርበታል ብለዋል።ኢሬቻ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ የሰላም የእርቅ እና የመሰባሰብ በዓል መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ የበዓሉ ተሳታፊዎችም ከአባ ገዳዎች የተላላለፈውን መልዕክት በመገንዘብ በአሉ በየአከባቢያቸው እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡

Published in አስተዳደር

2013 / የመስቀል ደመራ በዓል የሃይማኖት ዓባቶችና እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሁኔታ በመከበር ላይ ነው፡፡በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

Published in አስተዳደር

1. የወቅቱ ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው Covid-19 ወረርሽኝ በአገራችን እንዲሁም በከተማችን ከተከሰተበት ከመጋቢት ወር 2012 . ጀምሮ የህክምና አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በማስተባበር የተሠማሩ በከተማው አስተዳደሩ ስር በሚገኙ የጤና ተቋማት ሁሉ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ይህ ወረርሽኝ በአገራችን ስጋት መሆኑ እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ የከተማ አስተዳደሩ የገቢ ግብር ወጪያቸውን ለመሸፈን ውሳኔ አሳልፏል።

2. የከተሞች ዕድገት እና ልማት ከአካባቢያቸው ጋር ሲተሳሰር የህዝባችን የጋራ ተጠቃሚነት ፣የአብሮነት አስተሳሰብ እና ሰላማዊ ግንኙነትን ያዳብራል፡፡አዲስ አበባም በዙሪያዋ ካሉ አካባቢዎች ለእድገት እና ልማቷ ብዙ ግብዓቶችን እያገኘች እድገት እና መስፋፋቷም ሲፋጠን በዙሪያዋ ላሉ ነዋሪዎች ትሩፋት እንጂ መከራና መሰደድ መሆን የለበትም ፡፡

Published in አስተዳደር

 

የከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸውን ስራዎች በሰዓቱ እንደሚጨርስ ማሳያ የሆነው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ለመሩ ላስተባበሩ እንዲሁም የግንባታው ሂደት ላይ ለተሳተፉ አካላት የምስጋና የእራት ግብዣ ተደርጓል።የፕሮጀክቱ ግንባታ ሂደት ለሌሎች ፕሮጀክቶች ልምድ እና ተሞክሮ የሚሆን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ አዳነች በተለየ ፍጥነት እና ብርታት ፕሮጀክቱ በተባለው ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Published in አስተዳደር
Donderdag, 24 September 2020 07:38

ይህ ነው ኢትዮጵያዊነት!

ዛሬ ማለዳ የከተማ አስተዳደሩን የአብሮነት ጥሪ በመቀበል የከተማችን የጽዳት ሰራተኞች ከተለያዩ ቤተ እምነቶች የተገኙ የሃይማኖት መሪዎች እና የተለያዩ የእምነት ተከታይ ወጣቶችፍቅር ያሸንፋል" በማለት መስቀል አደባባይ ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግጁነቱ የተሟላ እንዲሆን የማጽዳት ስራ ሰርተዋል። በዚህ መልካም አራአያዊ ተግባር ላይ የተሳተፉትን ሁሉ ከልቤ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

Published in አስተዳደር

 

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ አቃቤ ህግን የመሩበት ወቅት በአንድ በኩል የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ የህግ የበላይነትን የሚገዳደሩ እንቅስቃሴዎች ፈተና የነበሩበት ነው ያሉት የተቋሙ አመራሮች ወይዘሮ አዳነች በሰጡት አመራር ተቋሙ ፈተናዎቹን ተቋቁሞ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡በተቋሙ አዲስ የስራ ባህል እንዲመጣ አድርገዋል ታታሪነታቸው እና ትጋታቸውም የሚደነቅ ነው ይላሉ የኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዮስ፡፡"የወይዘሮ አዳነች ትጋት ታታሪነት ስራ ወዳድነት እና መሰጠት በጣም የሚደነቅ ነው በደንብ ሰርተው የሚያሰሩ አመራር ናቸው፡፡ ለስራ ትልቅ መሰጠት ነው ነበራቸው ሰኞ ማክሰኞ ከእሁድ እስከ እሁድ ማታ እና ቀን ሁላችንም ያለንን 24 ሰዓት እንዴት እንደምንጠቀምበት ያሳዩን ናቸው፡፡ ለእኔ ሀገር መውደድ ይሄ ነው ብዙ ንግግር ማድረግ ሳይሆን እንደዚህ ተሰጥቶ ሌላውንም አስተባብሮ መስራት ነው ባለው ጉልበት እና አቅም ሀገር ወዳድነትን ጠንካራ የስራ በህል እና ዲሲፕሊንን አሳተውናል ስለዚህ እናመሰግናለን።"

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው በተቋሙ በነበራቸው ቆይታ መላው አመራር እና ሰራተኛ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው የህግ የበላይነትን ከማስከበር አንጻር የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎችን አመራር እና ሰራተኛው ከግብ እንዲያደርስ ጠይቀዋል፡፡

"ከእናንተ ጋራ በሰራሁባቸው ወራቶች ላደረጋችሁልኝ ትብብር አመራሬን ተቀብላችሁ የሰራነውን ያህል እንደንሰራ ላደረጋችሁት ጥረት ቅንነት ትጋት፣ ከልቤ ላመሰግናችሁ ወዳለሁ ፡፡ የህግ የበላይነትን ከማክበር እና ከማስከበር ጋራ በማህበረሰባችን ትልቅ ንቅናቄ መፈጠር አለበት የምንሰራቸው ስራዎች የእኛ ብቻ ሳሆኑ ሁሉም ሰው በባለቤትነት የሚይዘው እንዲደግፈን አብሮን እንዲቆም የህግ የበላይነት የመንግስት ተቋም ብቻ የሚሰራው አለመሆኑን እንደጠቅላይ አቃቤ ህግም ከሁሉም ተቋማት ጋር ተናበን ህግ ለማስከበር የያዝነውን እቅድ ተግባራዊ እንደምታደርጉት ሙሉ እምነት አለኝ "የህግ የበላይነት የህብረተሰቡ ዋነኛ ጥያቅ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ አዳነች ይህን የህዝብ ጥያቄ ለማርካት ሀላፊነት አለባችሁ እና ተግታችሁ ስሩ ሲሉም ሀሳባቸውን አካፍለዋል፡፡

Published in አስተዳደር

በአዲስ አበባ በየካቲት 27 /2011 ዓም. በተደረገው እጣ ማውጣት ስነ-ስርአት እጣ ወቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ ባለ ዕጣዎች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ በአፋጣኝ የሚፈፀም መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለፀ

=================

የከተማ አስተዳደሩ በየወቅቱ የሚነሱ የነዋሪዎቹን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የጋራ መኖርያ ቤቶች ጉዳይ የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ የበዛበት ሆኖ ቆይቶአል፡፡ በቀረበው የስራ ሪፖርት መሰረት ዕጣ ወቶላቸው በባለ እጣዎች እጅ ያልደረሱ ቤቶች መኖራቸውን ማወቅ ተችሎአል፡፡ይኃውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 40/60 እና 20/80 ፕሮግራሞች የተገነቡ ቤቶችን የካቲት 27/2011 / ዕጣ ማውጣቱ እና ሆኖም ቤቶቹ በቂ የመሠረተ ልማት በሌለባቸው የማስፋፊያ አካባቢዎች በመገንባታቸው እና በሚፈለገው ልክ አጠቃላይ የሳይት ስራው በወቅቱ ባለመጠናቀቁ ለባለ እድለኞች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን የከተማው አስተዳደርሩ ገልፆ እጣ ወቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ ባለ ዕጣዎች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ እንዲጀመር ወስኖአል።

Published in አስተዳደር