open

Items filtered by date: Februarie 2021

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል
Items filtered by date: Februarie 2021

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ 84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።በተጨማሪም የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡ ሲሆን በሰመዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል

Published in አስተዳደር

የፕሮጀክቱ አካል የሆነ እና ለትራፊክ ፍሰት እንዲሁም ለሰላም እና ጸጥታ ስራ የሚያግዙ 17 ፓትሮል ተሸከርካሪዎችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል፡፡በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ጥራቱ በየነ ተሸከርካሪዎቹን አስረክበዋል፡፡በመርሃ ግብሩ በኢትዮጰያ የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጀር ሚስስ ዳይና ፐትሪስኩ እንደገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እና የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል አለም ባንክ 200 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነድፎ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር / / ጌታሁን መኩሪያ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ /ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ መምህራን ጋር ውይይት አካሂደዋል ።ከመምህራን ጋር በተደረገው ውይይት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በሁሉም አቅጣጫዎች ከለውጡ መነሻ አንስቶ እዚህ እንዲደርስ ካደረጉት አካላት አንዱ አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰብ ነው ብለዋል ።ኢትዮጵያ ባለፉት 2 አመታት የጀመረችው ለውጥ ትኩረት የሀገረ መንግስት ግንባታ ነው ያሉት / አዳነች ይችን ሀገር ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር ሁሉም የራሱን አሻራ ሊያሳርፍ እንደሚገባ ተናግረዋል

Published in አስተዳደር

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸው 2039 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል ።በምረቃው ስነስርዓት ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ፣የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋልበ ምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ለተማሪዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በዩንቨርስቲ ቆይታችሁ ያሳለፋችኋቸው የደስታና የመከፋት ፤መውደቅና መነሳቶች ከመደበኛ ትምህርታችሁ ጎን ለጎን ችግርን የመጋፈጥ የህይወት ልምምድ ፣የመተሳስብ እና የመተባበር አቅም ያገኛችሁበት ሆኖ እንዳለፈ አምናለሁ ብለዋል ።የኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲን ጨምሮ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች በቀሰማችሁት የእውቀት ብርሃን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማንንም ሳይጠብቁ በመላው ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ የሀገርን ሰላም በመጠበቅ እና በሀቀኝነት ህዝብን በማገልገል በተግባር መለወጥ እንደሚገባ / አዳነች አቤቤ ገልጸዋል

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ እና ዘመናዊ የተባለውን እና በክብር / አበበች ጎበና ስም የተሰየመውን የእናቶች እና ህፃናት ሆስፒታል በይፋ አስመረቁ።ሆስፒታሉ 700 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን በውስጡ 400 በላይ አስተኝቶ መታከሚያ አልጋዎችን ያካተተ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት ለሰባት እናቶች በቀዶ ጥገና የማዋል አገልግሎት ይሰጣል

Published in አስተዳደር

"ታላቁ ህዳሴን ለመገንባት ሳናጠና አልገባንም፤ ሳንጨርስ አናቆምም፤የብልጽግና ጉዟችን በህዳሴ ምእራፍ ውስጥ የሚደምቅ የከተማችን ብሎም የሀገራችን ብርሃን ነው"ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤበዋንጫ ሽኝት መርሐግብር ላይ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ማደሪያ ላልነበረው ዓባይ ማደሪያውን ላበጃችሁ፤ ከታሪክ ተናጋሪነት ወደ ታሪክ ሰሪነት ላሸጋገራችሁን በአለም አደባባይ ለአባይ ሞግታችሁ፣ የጉባ በረሃ ንዳድን ተቋቁማችሁ፣ በክብር ከዚህ መድረክ ላይ እንድንቆም ላበቃችሁን ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች ከልብ የሆነ ምስጋናን አቀርባለሁ ብለዋል ፡፡ውድ የአገሬ ልጆች፤ በተለይም የአዲስ አበባችን ነዋሪዎች፤የመንግስት አመራሮችና ሰራተኞች የማመስገኛውን ቃል በተግባር በወርቅ ቀለም ስለጻፋችሁ፣ ከስንዝር እስከ እርምጃ፡ ሳትሰስቱ ለታላቅነታችን መገለጫ ለህዳሴ ግድባችን አሻራችሁን ማስቀመጥ በመቻላችሁ ነው ብለዋል / አዳነች ፡፡ዓባይ ወንዝ ብቻም አይደለም ይልቁንም አገር ነው ምክትል ከንቲባዋ ህዳሴ ግድብ ብቻም አይደለም ይልቁንም የኢትዮጵያ መድመቂያ አርማና ኩራት ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።ዓባይ ስም ብቻም አይደለም አሻጋሪ ሃሳብም ነው ዓባይ ብርሃን ብቻም አይደለም ምግብም ነው ለዚህም ነው እራትም መብራትም ነው የምንለው ሲሉ / አዳነች ገልጸዋል

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ አራዳ ክፍለ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 139 የቀበሌ ቤቶች በማስለቀቅ ለአቅመ ደካሞች፣ ረዳት ለሌላቸው እና ለአካል ጉዳተኞች በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡

የቀበሌ ቤቶቹን በማስተላለፍ መርሐግብር ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት በከተማ ህገወጥነትን በመከላከል እና የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስርዓትን ለማስፈን የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡በዛሬው ዕለትም በአራዳ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 139 አባዎራዎች እና አካል ጉዳተኞች የተላለፉት የቀበሌ መኖሪያ ቤት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት አንዱ ማሳያ መሆናቸውን / አዳነች ተናግረዋል፡፡

Published in አስተዳደር

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ከራሺያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ከተውጣጡ የዓለም አቀፍ የቢዝነስ ትብብር አባላት ጋር በተለያዩ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በተለይ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቲክ መናህሪያነቷ ባለፈ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያስመዘገበችው ባለው እድገት የበርካታ ቱሪስቶችን በመሳብ ላይ ያለች ከተማ መሆኗን የጠቀሱት አባላቱ በመንግስት እና በግል ዘርፍ ትብብር ላይ አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡የከተማዋን እድገት በሚያፋጥኑ የቴክኖሎጂ ፣የአገልግሎት ፣የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለመስራት ያላቸውን የቢዝነስ አማራጮች ለከፍተኛ አመራሮቹ ያብራሩት አባላቱ በአውሮፓ እና አፍሪካ ሀገራት 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራታቸውን አባላቱ ተናግረዋል፡፡

Published in አስተዳደር

ትርፍን ሳያሰሉ የተለያዩ ህብረቀለማት የያዙ ክሮችን አሰናኝተው በሚለፉ የጥበበኛ እጆች የሚመረቱት ጥበቦች የድምቀታችንና የማንነታችን ሚስጥር ናቸው፤ ሀገራችንም የህብረብሔሮቿን ሀሳብ ቋንቋ ባህልና እምነት በአንድ አሰናኝታ የምትፈካ የብዙሀን የአብሮነት ውበት ማሳያ ናት!" ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ 1ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የሽሮ ሜዳ የባህል አልባሳት መሸጫ የገበያ ማዕከልን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።በምርቃት መርሐግብሩ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት የገበያ ማዕከሉ በእንጦጦ ፓርክ አቅራቢያ በመሆኑ ለጉብኝት የሚመጡ ቱሪስቶች የባህል አልባሳቱን በማቅረብ በዘርፉ ለተሰማሩ ዜጎች የገቢ ምንጭ እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል

በገበያ ማዕከል ተጠቃሚ ወጣቶች ሕብረብሄራዊ፣ ደማቅ እና ውብ የሆነውን የኢትዮጵያዊ አልባሳትን የሚያጎላ በጥራት በማምረት ወደ ገበያው እንዲገቡ / አዳነች ጥሪ አቅርበዋል

Published in አስተዳደር

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የለውጥ አመራሩ ዘረፋና ሌብነትን ለመታገል በገባው ቃል መሰረት ምንም እንኳ ቢዘገይም የነዋሪውን ቅሬታ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት: በገለልተኛ አካል እና በተጨባጭ ጥናት ላይ በመመርኮዝ ማጣራቱ ይታወቃል፡፡የተደረገውን ጥናት ግኝት መነሻ በማድረግ መወሰድ አለበት ባሉት እርምጃ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ ተወያይተዋል፡፡

1. በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች የከተማ አስተዳደሩ እንዲወርስ እና በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ገቢው ለህዝብ ልማት እንዲውል፤

2. በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ : ባዶና ዝግ ሆነው የተቀመጡ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን 1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤

Published in አስተዳደር