open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/የቀጣይ አመት የተማሪዎች ዩኒፎርም

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ የታሪክ ተመራማሪ እና ደራሲ / ፍቅሬ ቶሎሳ ጋር ውይይት አካሂደዋል።/ ፍቅሬ ቶሎሳ ለአመታት በታሪክ እና በስነፅሁፍ ዘርፍ ሀገርን እና ትውልድን በትብብር መገንባት የሚያስችሉ ስራዎችን በመሰራት ላይ ይገኛሉ ያሉት ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በቢሮዋቸው ተገኝተው ላበረከቱት የመፅሐፍት ስጦታ እና ለነበራቸው ፍሬያማ ውይይት ምስጋናቸውን አቅርበዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጥናቱ ከተለየ 1,338 ሄክታር መሬት ውስጥ 1,050 ሄክታር ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ የተደረገ መሆኑን / ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።የአዲስ አበባ ከተማ / ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንዳመላከቱት በከተማዋ በህገ-ወጥ ወረራ የተያዘው መሬት 1,338 ሄክታር ሲሆን በገንዘብ ሲተመን 14 ቢሊየን ብር የሚገመት መሆኑንና የህዝብና የመንግስት ሀብት በሪል ስቴት አልሚዎች፣ በግለሰቦች፣ በሀይማኖት ተቋማትና በቡድን በመደራጀትና መንደር በመመስረት ጭምር በሚገለፅ መልኩ የመሬት ወረራ ተፈፅሟል፡፡

በወረራ ከተያዘውና በጥናቱ ከተለዩ 1,338 ሄክታር መሬት ውስጥ 1,050 ሄክታር የሚሆን መሬት እንዲፀዳ በማድረግ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደርጓል።ወ/ አዳነች አቤቤ አክለው የቀረው መሬት በቀጣይ የከተማውን ልማት በሚያረጋገጥ መልኩ በሊዝና ለትልልቅ የልማት ስራዎች በጨረታ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል ብለዋል፡፡በህገወጥ መልኩ የተያዙ የጋራ መኖርያ ቤቶችን አስመልክቶ በማስለቀቅ ተጠቃሚ ለመሆን ተመዝግበው ለሚገኙ ዜጎች የማስተላለፍ ስራ እንዲሁም የቀበሌ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችንም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን በሚያሰፍን አግባብ እንዲፈፀም ይደረጋል ሲሉ / አዳነች ገልፀዋል፡፡