open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/ምክትል ከንቲባዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያከሩጫና ከስፖርትነት ባለፈ የአብሮነት ፣የስኬት ፣የፍቅር እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን የሃገራችንን ገጽታ ገንብቷል "ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

20ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ

በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 20ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደወትሮዉ በድምቀት፣ አዝናኝ እና አስደሳች በሆነ መልክ በከተማችን እየተካሄደ ይገኛል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሩጫና ከስፖርትነት ባለፈ የአብሮነት ፣የስኬት ፣የፍቅር እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን የሃገራችንን ገጽታ ገንብቷል ብለዋል ።እኛም እንደሩጫው ሁሉ ሃገራችን በምታደርገው ድህነትን የማሸነፍ፣ ዘላቂ እድገትን የማስመዝገብ እና የታላቅነት ጉዞ በየእለት ኑሮአችን አሸናፊዎች እንሁን ሲሉ / አዳነች መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ የኔትወርክ፣ የሴኪዩሪቲ፣ የኢንተርኔትና ዋይፋይ፣ የአይፒ ቢኤክስ፣ የወረፋ ማስጠበቂያ ሲስተም፣ የዳታ ሴንተር የከተማ አቀፍ ሜይል ሲስተም ሌሎች መሰል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ስራ አስጀምረዋል ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የምንገኝበት ወቅት አለም በቴክኖሎጂ አንድ የሆነበት በመሆኑ በከተማችንም ደህንነቱ እና ጥራቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂ ማበልጸግ እና መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል አገልግሎት መስጫ የዲጂታል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ተግባራዊ መሆን አገልግሎት ፈላጊውን አካል የጊዜ፣ የጉልበት እና እንግልት ከማስቀረቱም ባለፈ ሙስናን እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከታተል ፋይዳው የጎላ መሆኑን ምክትል ከንቲባ / አዳነች ተናግረዋል