open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደመቀ መኮንን እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ሚኒስትሮችን ጨምሮ፣የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የተለያዩ የስፖርት ፌዴሬሽን አመራሮች በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጪው 10 ዓመት የከተማዋን ዘላቂ ልማት እና እድገት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ዙሪያ 10 ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ከሁሉም የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በውይይት መድረኩ ላይ ከተማ አስተዳደሩ የሀገራችንን የብልፅግና ትልም ዕውን ለማድረግ ከወጣው ዕቅድ የተቀዳ 10 አመት መነሻ ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።መዳረሻ ዕቅዱ የተሟላ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች ፍላጎት ያካተተ እንዲሆንም በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በማድረግ ጠቃሚ ግብአት ማሰባሰብ አስፈላጊ መሆኑንም አቶ ጃንጥራር ጠቅሰዋል።