open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ የግል ድርጅቶች ባለቤት የሆኑ ባለሃብቶች "ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት 390 ሚሊየን ብር ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በተገኙበት አስረክበዋል፡፡በመርሃግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በዚህ ሃገር አቀፍ የልማት አጀንዳ ቃል ገብተው በተግባርም ለተሳተፉት ባለሃብቶች "ሁሌ ስንጠራችሁ የማናጣችሁ ለሀገርና ለትውልድ ለሚተርፍ መልካምነት እና ቸርነት የምትተጉ" በማለት በራሳቸውና በግል ድርጅቶች የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ /ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር ሊዮ ዩሺ እና ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በአዲስ አበባ ስለሚገነቡት የአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክቶች እና ተያያዥ የትብብር ስራዎች ዙርያ ተወያይተዋል።በውይይታቸው በአዲስ አበባ ስለሚገነቡት የአፍሪካ መንደር ፕሮጀክት እና የሲ.. አፍሪካ ዋና መስሪያ ቤት እውን የማድረግ የትብብር አቅጣጫ ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።