open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ አራዳ ክፍለ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 139 የቀበሌ ቤቶች በማስለቀቅ ለአቅመ ደካሞች፣ ረዳት ለሌላቸው እና ለአካል ጉዳተኞች በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡

የቀበሌ ቤቶቹን በማስተላለፍ መርሐግብር ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት በከተማ ህገወጥነትን በመከላከል እና የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስርዓትን ለማስፈን የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡በዛሬው ዕለትም በአራዳ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 139 አባዎራዎች እና አካል ጉዳተኞች የተላለፉት የቀበሌ መኖሪያ ቤት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት አንዱ ማሳያ መሆናቸውን / አዳነች ተናግረዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ከራሺያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ከተውጣጡ የዓለም አቀፍ የቢዝነስ ትብብር አባላት ጋር በተለያዩ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በተለይ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቲክ መናህሪያነቷ ባለፈ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያስመዘገበችው ባለው እድገት የበርካታ ቱሪስቶችን በመሳብ ላይ ያለች ከተማ መሆኗን የጠቀሱት አባላቱ በመንግስት እና በግል ዘርፍ ትብብር ላይ አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡የከተማዋን እድገት በሚያፋጥኑ የቴክኖሎጂ ፣የአገልግሎት ፣የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለመስራት ያላቸውን የቢዝነስ አማራጮች ለከፍተኛ አመራሮቹ ያብራሩት አባላቱ በአውሮፓ እና አፍሪካ ሀገራት 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራታቸውን አባላቱ ተናግረዋል፡፡