open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

ትርፍን ሳያሰሉ የተለያዩ ህብረቀለማት የያዙ ክሮችን አሰናኝተው በሚለፉ የጥበበኛ እጆች የሚመረቱት ጥበቦች የድምቀታችንና የማንነታችን ሚስጥር ናቸው፤ ሀገራችንም የህብረብሔሮቿን ሀሳብ ቋንቋ ባህልና እምነት በአንድ አሰናኝታ የምትፈካ የብዙሀን የአብሮነት ውበት ማሳያ ናት!" ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ 1ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የሽሮ ሜዳ የባህል አልባሳት መሸጫ የገበያ ማዕከልን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።በምርቃት መርሐግብሩ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት የገበያ ማዕከሉ በእንጦጦ ፓርክ አቅራቢያ በመሆኑ ለጉብኝት የሚመጡ ቱሪስቶች የባህል አልባሳቱን በማቅረብ በዘርፉ ለተሰማሩ ዜጎች የገቢ ምንጭ እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል

በገበያ ማዕከል ተጠቃሚ ወጣቶች ሕብረብሄራዊ፣ ደማቅ እና ውብ የሆነውን የኢትዮጵያዊ አልባሳትን የሚያጎላ በጥራት በማምረት ወደ ገበያው እንዲገቡ / አዳነች ጥሪ አቅርበዋል

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የለውጥ አመራሩ ዘረፋና ሌብነትን ለመታገል በገባው ቃል መሰረት ምንም እንኳ ቢዘገይም የነዋሪውን ቅሬታ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት: በገለልተኛ አካል እና በተጨባጭ ጥናት ላይ በመመርኮዝ ማጣራቱ ይታወቃል፡፡የተደረገውን ጥናት ግኝት መነሻ በማድረግ መወሰድ አለበት ባሉት እርምጃ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ ተወያይተዋል፡፡

1. በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች የከተማ አስተዳደሩ እንዲወርስ እና በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ገቢው ለህዝብ ልማት እንዲውል፤

2. በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ : ባዶና ዝግ ሆነው የተቀመጡ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን 1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤