ለማህበረሰቡ ወቅታዊና ተአማኒነት ያለውን መረጃ ይሰበስባል : ያደራጃል እንዲሁም ያሰራጫል
የካቢኔ አጀንዳዎች ከመሰብሰብ ጀምሮ እስከ ቅድሚያ መስጠትና መፍትሄ መፈለግ
በማህበራዊ, ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዓላማዎች ላይ የተመሠረተ ውጭ አገር ከተማዎች ጋር ሽርክና ማቋቋም.
አዎንታዊ ለውጥ ለመገንባት አለም አቀፍ ስብሰባዎችንና አውደ ጥናቶች ያደራጃል
የእቅድ ትግበራ ምዘናና ክትትል ማስፈጸም
የእቅድ ትግበራ ያደራጃል ይመረምራል
ዋና ዋና የከተማዋ መልካም አስተዳደርና የልማት ለውጦችን በህትመትና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በኩል ለህብረተሰቡ ማስተዋወቅ
በዳያስፖራ ጉዳዮች ላይ መረጃ ይሰበስባል ያዘጋጃል ይሰጣል
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በለውጡ የተመለሱ የአርሶ አደሩ ጥያቄዎች በቀጣይ ምላሽ በሚያገኙባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የአርሶ አደር ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በውይይቱ ሁሉን አቀፍ ፣አካታች ፣ አንዱን ጠቅሞ አንዱን የማይገፋ የሚለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በከተማችን ተከማችቶ የቆየውን የአርሶ አደሩን ጥያቄ በመመለስ እውን መሆን መጀመሩን አስረድተዋል።
አርሶአደሩ በግል፣ ተደራጅቶ እንዲሁም አቅም የሌላቸው ደግሞ ይዞታቸውን በማያጡበት አግባብ አቅም ካላቸው ጋር መስራት የሚያስችላቸው መመሪያ መውጣቱን ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል።የአርሶአደር ተወካይ ኮሚቴዎች ለወከላቸው አርሶ አደር ታማኝ ሆነው ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እንዲረባረቡ እና አርሶአደሩ በስሙ የሚነግዱ ደላሎችን ሊታገላቸው እንደሚገባም ወ/ሮ አዳነች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አርሶአደሩ ከተማ መጣብን ሳይሆን መጣልን ብሎ እንዲያስብ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
Read more...“ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያከሩጫና ከስፖርትነት ባለፈ የአብሮነት ፣የስኬት ፣የፍቅር እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን የሃገራችንን ገጽታ ገንብቷል "ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
20ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ
በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 20ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደወትሮዉ በድምቀት፣ አዝናኝ እና አስደሳች በሆነ መልክ በከተማችን እየተካሄደ ይገኛል። “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” ከሩጫና ከስፖርትነት ባለፈ የአብሮነት ፣የስኬት ፣የፍቅር እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን የሃገራችንን ገጽታ ገንብቷል ብለዋል ።እኛም እንደሩጫው ሁሉ ሃገራችን በምታደርገው ድህነትን የማሸነፍ፣ ዘላቂ እድገትን የማስመዝገብ እና የታላቅነት ጉዞ በየእለት ኑሮአችን አሸናፊዎች እንሁን ሲሉ ወ/ሮ አዳነች መልዕክት አስተላልፈዋል።
Read more...አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ህብረት ዋና መ/ቤት መቀመጫ ስትሆን በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ ባላት ታሪካዊ , ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ትርጉም "የአፍሪካ ዋና ከተማ" የሚል ስያሜ አሰጥቶአታል። የአፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤትም ከተማይቱ ውስጥ ማግኘት ይቻላል.
ከእንጦጦ ተራሮች ግርጌ ስር የምትገኝ ሲሆን ከባሕር ወለል በላይ 7.726 ጫማ (2,355 ሜትር) በዓለም ውስጥ ሶስተኛው ከፍተኛ ዋና ከተማ ናት.በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥዋ በአገሪቱ ማዕከላዊ ስፍራ ውስጥ ትገኛለች።
Rating:በ 2007 ዓ.ም በተደረገ ቆጠራ ከ 3.627.934 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ያላት አዲስ አበባ በዓለም ካሉ በመሬት ከተከበቡ ሀገራት ትልቋ ዋና ከተማ ናት፡፡
ከአለም ውብ ከተማዎች መካክል የምትጠቀሰው ይች ከተማ በታሪክ በጣም ጉልህ የሆነ ስፍራ አላት።
Rating: